በቾ ወሊሶ የገበሬዎች ሕብረት ስራ ዩኒየን የተለያየ ዓይነት ያገለገሉ የእርሻ ትራክተሮች፣ የቮልቮ መኪና ተሳቢ፣ የዘር መዝሪያ ማሽን፣ የእህል መውቂያ ማሽኖች እና የተለያዩ ዓይነት አሮጌ ሞተር ሳይክሎች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ለሦስተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በቾ ወሊሶ የገበሬዎች ሕብረት ስራ ዩኒየን የተለያየ ዓይነት ያገለገሉ የእርሻ ትራክተሮች፣ የቮልቮ መኪና ተሳቢ፣ የዘር መዝሪያ ማሽን፣ የእህል መውቂያ ማሽኖች እና የተላዩ ዓይነት አሮጌ ሞተር ሳይክሎች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም እነዚህን መግዛት የሚፈልጉ ግለሰብ ወይም ድርጅት ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን መስፈርቶች በማሟላት ተወዳድሮ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መመዘኛዎች፡-
1. ለጨረታ ሰነድ ግዢ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በዩኒየኑ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000087184327 ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ወይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000036818348 በመክፈል ሰነዱን ከዩኒየን መውሰድ አለባቸው።
2. ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ማስያዣ ያቀረቡትን ዋጋ 5% በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ሰነድ ማስያዝ አለባቸው።
3. ተጫራቾች ይህ ጨረታ ከወጣ ቀን ጀምሮ እስከ 29/08/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዶቹን በታሸገ ኤንቨሎፕ ዘወትር በሥራ ሰዓት ዩኒየኑ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
4. የጨረታ መክፈቻ ቀን በ29/08/2018 ዓ.ም ሳጥኑ ከጠዋቱ በ5፡00 ሰዓት ተዘግቶ 5፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
5. ተጫራቾች አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።
6. ዩኒየኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
7. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈውን ንብረት ሙሉ በሙሉ እስከ 10 ቀን ጊዜ ውስጥ ማንሳት ይኖርበታል።
- አድራሻ፡- በጅማ መንገድ ከአዲስ አበባ 80ኪ.ሜ ቱሉ ቦሎ ከተማ ላይ እንገኛለን።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር 0911080003/0912122971 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን በቾ ወሊሶ የገበሬዎች የሕብረት ሥራ ዩኒየን ኃላ/የተ/ማህ
Tender details
- Deadline: 2026-05-07
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-05-07 11:30
- Region: Oromia
- Publishing entity: Becho-Woliso Farmers Cooperative Union
- Buyer address: በጅማ መንገድ ከአ/አበባ 80 ኪ.ሜ ርቀት ቱሉቦሎ ከተማ ላይ እንገኛለን
- Bid bond: 5%
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published: Apr 20, 2026
- Posted at: 2026-04-21T08:22:30.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.