የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ በ2018 ዓ.ም የሹፌር፣ የጽዳትና ተላላኪ የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰፋት ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 009-2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ በ2018 ዓ.ም የሹፌር፣ የጽዳትና ተላላኪ የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰፋት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟስ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ይፈልጋል።
1. ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ፣ ንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ወቅታዊ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ለም ሆቴል አካባቢ ኤም ኤ ህንጻ 10ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10-04 ከፋይናንስና ክፍያ ዳይሬክቶሬት ክፍል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ 3000.00 (ሶስት ሺህ) ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የስፌት ዋጋ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት 10ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10-08 የግዥ ዳይሬክቶሬት ከፍል ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዋናውንና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው በ11ኛዉ የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ጠዋት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
6. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ለም ሆቴል አካባቢ ኤም ኤ ህንፃ 10ኛ ፎቅ እንገኛለን።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 13 75 51 10/ 09 13 72 75 49
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-05-01
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛዉ የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-01 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛዉ የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa City Administration Planning and Development Bureau
- Bid bond: 3000.00 (ሶስት ሺህ ብር)
- Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
- Published: Apr 20, 2026
- Posted at: 2026-04-21T08:49:54.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.