በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚኒስቴር የተለያየ ሞዴል ያላቸው 12 ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚኒስቴር በታክስ ዕዳ የያዛቸውን የተለያዩ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎችን ለመሸጥ የወጣ የግልጽ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁ- 05/2018 የሚኒስቴር መ/ቤቱ ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን የታከስ ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመክፈላቸው ምክንያት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41 በተሠጠው ስልጣን መሠረት ከምቾት ዳይፕር ማምረቻ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፣ ከአረብ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር፣ ዮዥን ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር፣ ከሜጋ ሶርስ ኃ/የተ/ የግ/ማህበር እና ከኤድናሞል EHTS ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተያዙ የተለያየ ሞዴል ያላቸው 12 ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም፦
1. በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ማንነቱን የሚገልጽ የነዋሪነት መታወቂያ (ፓስፖርት)ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኢንቨሎፕ በማሸግ ለግልፅ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የግልፅ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00ሰዓት ህንፃ “ለ” 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ከግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ህንፃ “ሀ” 2ኛፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ከታክስ ዕዳ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ መውሰድ ይኖርበታል።
3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ንብረቶች የሰጡትን ዋጋ 1/10ኛውን ብቻ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በገቢዎች ሚኒስቴር ስም (Ministry of Revenue) በባንክ አሰርተው ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት ሰነድ ገዝተው መጫረት ይችላሉ።
|
ተቁ |
የመ/ቤቱ ስም |
ለጨረታ የቀረበው የንብረት ዓይነት |
የንብረቶቹ መመልከቻ ቀን |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ገቢዎች ሚስቴር |
የተለያየ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎች |
ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት |
ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 15 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 16ኛ ቀን 3፡45 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4፡00 ሰአት ይከፈታል፡፡ |
5. የጨረታ መክፈቻ ቦታ፡- መገናኛ በሚገኘው በሚኒስቴር መ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች/ ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል ።
6. የግልፅ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ 16ኛው ቀን የመ/ቤቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን የግልፅ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ ቀን ይሆናል።
7. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር እንደ አስፈላጊነቱ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የግልፅ ጨረታ ኮሚቴው መረጃውን አጣርቶ እንደጨረሰ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
8. የተሽከርካሪ ጨረታ ለሚያሸንፉ ተጫራቾች ከስመ-ንብረት ዝውውር ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ወጪዎች (የቦሎና ሌሎች ተጓዳኝ ወጪዎች) ሻጭን አይመለከትም።
9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ መ/ቤቱ በሚሠጠው አድራሻ ገቢ በማድረግ ያሸነፋበትን ሀብት ንብረት መረከብ ይኖርባቸዋል።
10. ከላይ በተ/ቁ 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ በማድረግ ንብረታቸውን ያልተረከቡ ተጫራቾች የግልፅ ረታው ተሠርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በCPO ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ንብረቱ እንዳልተሸጠ ተቆጥሮ በቀጣይ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
11. ሚኒስቴር መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ የግልፅ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-617-84-90 ኮድ(2044)(2045) (2046) የውስጥ መስመር ( EXT) 2044ደውለው
መጠየቅ ወይም የተቋሙን ዌብሳይት WWW.MOH.Gov.et መመልከት ይቻላል።
ገቢዎች ሚኒስቴር
Tender details
- Deadline: 2026-05-05
- Bid closing time: 09:45
- Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 15 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 16ኛ ቀን 3፡45 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-05 10:00
- Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 15 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 16ኛ ቀን 4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ministry of Revenue
- Buyer address: የቀድሞ ቡና ቦርድ ከንፋስ ስልክ ት/ቤት ዝቅ ብሎ ባለው ሙለጌ ህንፃ ላይ
- Bid bond: 1/10ኛውን
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: Apr 20, 2026
- Posted at: 2026-04-21T09:16:51.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.