የኢትዮጵያ ብቃትና ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ልዩ ልዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 13/18

የኢትዮጵያ ብቃትና ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ልዩ ልዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ አዲስ አባባ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 ሽያጭ ክፍል በመክፈል ደረሰኝ ይዘው ቢሮ ቁጥር 208 ከአቅርቦትና ኮንትራት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

3. ንብረቶችን ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የገዙበትን ደረሰኝ በመያዝ አዲስ አበባ ዋና ግቢ በመገኘት ዘወትር በስራ ሰዓት ማየት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የሚገዙትን ያገለገሉ ተሽከርካሪ የጨረታ መነሻ ዋጋ 2 በመቶ (2%) የጨረታ ማስከበሪያ በኢንስቲትዩቱ ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

5. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ይውል እና በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።

6. የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል። ተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ ቢቀሩ የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፤

7. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው።

8. ልዩ ልዩ ንብረቶች የመነሻ ዋጋ 2 በመቶ (2%) ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።

9. ኢንስቲትዩቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል።

10. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ በመክፈል ማንሳት ይኖርባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኢንስቲትዩቱ ገቢ ይደረጋል።

11. ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን እንደአስፈላጊቱ በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ከሳሊህተ ምህረት ማርያም ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት የሚገኘው ህንፃ

ስልክ ቁጥር 011 645 4147 / 011 645 3598 / 011 869 4931

ኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-06
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ይውል እና በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-06 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ይውል እና በ16ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Management Institute
  • Buyer address: ከሳህሊተ ምህረት ማርያም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት የሚገኘው ህንፃ
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Apr 21, 2026
  • Posted at: 2026-04-21T09:51:40.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders