በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የቲሊሊ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እንዲሁም የኮንስትራክሽን እቃዎች በሎት ድምር አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የቲሊሊ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

  • ሎት 1. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እንዲሁም
  • ሎት 2 የኮንስትራክሽን እቃዎች በሎት ድምር አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተለትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡

3. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ቲሊሊ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚወዳደሩበት ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡

7. የመጫረቻ ሰነዱን በመግዛት እና በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በማድረግ የቲሊሊ ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ተከታታይ ቀናት 4፡00 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪልቻቸው) በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ዕለት በዓል (ዝግ) ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡

8. አሸናፊው የሚለየው መስፈርቱን ያሟላ በየሎቱ በዝቅተኛ ዋጋ የሞላ ነው፡፡

9. ጨረታውን 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

10. አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም ይኖርበታል፡፡

11. አሸናፊው ውሉን ከፈጸመ በኋላ እቃዎችን ቲሊሊ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ መጓጓዝ አለበት፡፡

12. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

13. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ የቲሊሊ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 47 05 38 52 /09 10 73 53 62 በመደወል ዝርዝር መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የቲሊሊ ከተማ አስተዳር ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-05
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-05 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በ16ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Tilili City Administration Finance Office
  • Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺ ብር)
  • Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: Apr 20, 2026
  • Posted at: 2026-04-21T10:01:55.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders