በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ በወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ስር የሚገኘዉን የሀይቅ ክሬሸር ከነበረበት ቦታ ነቅሎ ወደ አዲስ ቦታ ማስተከል ይፈልጋል
Description
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 01
በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ በወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ስር የሚገኘዉን የሀይቅ ክሬሸር ከነበረበት ቦታ ነቅሎ ወደ አዲስ ቦታ ማስተከል ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት ከዚህ በታች ሊያሟሉ የሚገባቸውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ ስስሆነም፡-
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ያላቸው እንድሳተፍ ይፈልጋል።
2. ተጫራቾች ሰነዱን ጨረታው ግልጽ ጨረታ ከወጣበት ከ17/11/2018 እስከ 1/12/2018/ ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 300.00/ ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ስዓት ደሴ በሚገኘው በጥገና ጽ/ቤቱ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋው 2% በባንክ የተረጋገጠው ቼክ /ሲፒኦ/ ለመ/ቤቱ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
4. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ምዝገባ ማስረጃ የዋናውን ፎቶ ኮፒ በማያያዝ በፓስጣ አሽገው እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ በጥገና ጽ/ቤቱ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት በታሽገ ኢንቭሎፕ ፖስታው ላይና በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተምና አድራሻ ፊርማ በማድረግ ለመስሪያ ቤቱ ማቅረብ አለባቸው።
6. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ስዓት ላይ ተዘግቶ በዚህ ቀን 4፡30 ላይ በጥገና ጽ/ቤቱ ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም የጨረታ ሰነዱ የተሟላ ከሆነ ይከፈታል።
7. አሸናፊ ተጫራች ከታወቀ በኋላ ለመልካም የስራ አፈፃፀም ዋሰትና የጠቅላላ ዋጋውን 10% የተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ለመ/ቤቱ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
8. ተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት ቼክ/ሲፒኦ/ ወዲያውኑ ይመለስለታል።
9. ጥገና ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ያወጡት ወጭ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም።
10. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ ከሰዓት እሁድ ወይም የባዕል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
11. በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ
በፋክስ ቁጥር 033-111-44-23 በመላክ ወይም
ስልክ ቁጥር 033-111-62-29
ፖ.ስ.ታ 60
በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ
Tender details
- Deadline: 2026-08-08
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-08 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Amhara Rural Roads Construction Agency
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት
- Published: Jul 24, 2026
- Posted at: 2026-07-24T07:55:11.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.