ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ.የተ.የግ.ማህበር የኮንስትራክሽን ግብዓት፣ የሲሚንቶ ማጓጓዝ፣ ለቁፋሮ አገልግሎት የሚውሉ ሀመር እና ቢቶች፣ የኤሌክትሮ ሜካኒካል እቃዎች እንዲሁም የአልትራሶኒክ ፊቲንጎች (ultrasonic level transmitter) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ለኩባንያችን ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች የተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውል የኮንስትራክሽን ግብዓት፣ የሲሚንቶ ማጓጓዝ፣ ለቁፋሮ አገልግሎት የሚውሉ ሀመር እና ቢቶች፣ የኤሌክትሮ ሜካኒካል እቃዎች እና የአልትራሶኒክ ፊቲንጎች (ultrasonic level transmitter) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

.

ሎት

የእቃው አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ

የማቅረቢያ ቀን

1

01

የኮንስትራክሽን ግብዓት እቃዎች

100,000.00

20-35 ቀናት

2

02

የስሚንቶ ማጓጓዝ

100,000.00

እንደ አስፈላጊነቱ

3

03

ለቁፋሮ አገልግሎት የሚውሉ ሀመር እና ቢቶች

100,000.00

ከስቶክ

4

04

የኤሌክትሮ ሜካኒካል እቃዎች

150,000.00

ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት

5

05

የአልትራሶኒክ ፊቲንጎች (ultrasonic level transmitter)

50,000.00

 

30 ቀን

 

ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ አቅራቢ ድርጅት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት  www.tisisat.com  ማግኘት ይችላል።

የተጫራቾች መመሪያ፡-

1.ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምሰክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የTIN ሰርተፊኬት፣ በዘርፉ ለመሰማራት የተሰጣቸውን ፈቃድ እና ተያያዥነት ያላቸውን ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

2. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ ቴዲ የአሸከርካሪዎች ማሰልጠኛ ጎን በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisisat.com  ማግኘት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሰንጠረዥ የተመለከተውን ገንዘብ በCPO ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ ለገዥ የሚከፈል (unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው።

5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያወጡት ወጪ በተጫራቹ የሚሸፈን ይሆናል።

6. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን እና ቴክኒካል ሰነዳቸውን ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ ለእያንዳንዱን እቃ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል ሞልተው በግልፅ ማስቀመጥአለባቸው።

7. ይህ ጨረታ በኩባንያችን የግዥ መመሪያ ሰኔ 25 PR 03/2017/ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል። ዝርዝር የጨረታ መመሪያዎችን በሚዘጋጀው የጨረታ ሰነደ መስረት ማየት ይጠበቅባቸዋል።

8. ኩባንያው በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው መጠን 25% ቢጨምር ወይም ቢቀንስ የጨረታ አሸናፊው ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።

9. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ05 ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋውን 10 % የውል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (unconditional Bank Guarantee) በማሰራት ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።

10. የማቅረቢያ ጊዜ ከላይ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው መሠረት መሆን አለበት። የአቅራቢዎች ዋጋ ቢያንስ ለ90 ቀናት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ጸንቶ መቆየት አለበት።

11. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. ዕቃዉ ወይም አገልግሎቱ የሚቀርብበት ቦታ ሰነዱ ላይ በተገለው መሰረት።

13. ማሳሰቢያ፡- እንደ ኩባንያችን ፍላጎት ውድድሩ በሎት ወይም በእያንዳንዱ እቃ ነጠላ ዋጋ መሠረት ሊሆን ይችላል።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 058-220-4826 /058-320-2548/ በፋክስ ቁጥራችን 058 220 4830 መጠየቅ ይችላሉ።

ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-07-11
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-11 15:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Tis Esat Water Works P.L.C
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published: Jun 27, 2026
  • Posted at: 2026-06-27T07:56:55.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders