Construction machinery and plant
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬድዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የግልፅ ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬድዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ከዚህ በታች የተገለጸውን የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የመሣሪያው ዓይነት |
ብዛት |
ምርመራ |
|
1 |
Concrete Mixer Technical Specification For Concrete Mixer
|
1 |
|
ስለሆነም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰአት የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ) ብር በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ድራዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000322267979 ገቢ በማድረግ ድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ቢሮ ግዥ ክፍል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ስለሆነም ከታች የተዘረዘሩትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።
ማሳሰቢያ
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ ከገቢዎች ባለስልጣን ማቅረብ አለባቸው።
- በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኢጀንሲ በመንግሥት የዕቃና አገልግሎት አቅራቢነት በኤጀንሲው ድህረ ገፅ የተመዘገቡበትን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ ሲፒኦ ወይም ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ይዘጋል። በዚሁ ዕለትም ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አካባቢ በሚገኘው በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት የመሰብሰቢያ አዳራሽ የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን።
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፦
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ
- ለበለጠ መረጃ የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።
- ስልክ ቁጥር 025111-13-13 /0927636126/0919008017/
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬድዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
Tender details
- Deadline: 2026-08-18
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት
- Bid opening: 2026-08-18 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰአት
- Region: Dire Dawa
- Publishing entity: Ethiopian Roads Administration Dire Dawa Road Maintenance District
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Jul 31, 2026)
- Posted at: 2026-07-31T08:20:47.000Z