በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ለተቋሙ መገልገያ የሚሆን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ በሎት መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አብክመ/ሲዥቤምአ/ብ/ግ/ጨ/03/2018 ዓ/ም

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ለተቋሙ መገልገያ የሚሆን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ በሎት መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም  የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡

3. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ) በመክፈል ከግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይቻላል፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩባቸው የተለያዩ ምድቦች ወይም ሎቶች አንድ በመቶ ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም የሚያስይዙት ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በአብክመ ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት የተሰጠ ሕጋዊ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡

8. ተጫራቾች የቴክኒካል እና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን በተለያዩ ሁለት ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ከአንድ ቴክኒካል እና ከአንድ ፋይናንሻል ኦሪጅናል በተጨማሪ አንድ ቅጅ ቴክኒካል እና አንድ ቅጅ ፋይናንሻል በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት በግዥና ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 07 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሪክቶሬት ቢሮ ቁጥር 07 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ቀኑ በዓል ወይም የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

11. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 3158 ፋክስ 058 320 1183 ፖ.ሳ.ቁ 965 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

የአብክመ ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-05
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
  • Bid opening: 2026-05-05 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Apr 20, 2026
  • Posted at: 2026-04-21T10:23:36.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders