በአማራ ክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን G+3 የቢሮ አገልግሎት የሚውል ህንጻ ግንባታ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውን በግልጽ ጨረታ አዉጥቶ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግንባታዉን ማስገንባት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን G+3 የቢሮ አገልግሎት የሚውል ህንጻ ግንባታ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውን በግልጽ ጨረታ አዉጥቶ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግንባታዉን ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ 

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የዘርፉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

ስለሆነም፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)፣ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ኦርጅናልና ኮፒ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆኑ የተጨማሪ ሴት ታስክ (ቫት) የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡ የሚሙሉትም ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማያያዝ አለባቸው፡፡

4. የሚወዳደሩ ተጫራቾች የሥራ ደረጃቸው BC-4/GC-5  እና ከዚያ በላይ  ደረጃ ያላቸው፡፡

5. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛዉም ተጫረች  የጨረታ ሰነዱን በአማራ ክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን  ቢሮ ቁጥር 11 እራሳቸው ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የስራ ፈቃዳቸውን በማሳየት ብር 1500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን እና የንግድ ፈቃድ መረጃቸውን ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻው በፖስታ  በጥንቃቄ  በማሸግ  በአማራ ክልል ማረሚያ ቤት  ኮሚሽን  ቢሮ ቁጥር 11    ለዚሁ ጨረታ  በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት አለባቸው፡፡

7. የጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት  የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ታሽጎ ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት አያስተጓጉለውም፡፡ 16ኛው ቀን  የበዓል ቀን ከሆነ ለቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታ፡፡

8. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው የሥራ ዝርዝር መግለጫው መሰረት በሰነዱ በእያንዳንዱ በግልጽ ዋጋውን መሙላት እና የድርጅታቸውን አድራሻ፣ ስም፣ ማህተምና ፊርማ ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡

9. ተጫራቾች በሞሉት በነጠላ ዋጋ እና በጠቅላላ ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውጪ እንደሚሆኑ ማወቅ አለባቸው፡፡

10. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ካሉ በክልሉ የግዥ አዋጅ 179/2003 እና በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ከጨረታ ውጭ እንደሚደረጉ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ እንደሚደረግ እና በተመሳሳይ ሌላ ጨረታ እንዳይሳተፉ ይደረጋል፡፡

11. ተጫራቾች የጨረታ ውድድሩ በጠቅላላ ድምር ዋጋ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡

12. .ተጫራቾች በጨረታው ውጤት ቅር ከተሰኙ የጨረታ ውጤቱ በማስታወቂያ ቦርድ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅሬታቸውን በአማራ ክልል ማረሚያ ቤት  ኮሚሽን  ቢሮ ቁጥር 11 ማቅረብ ይችላሉ፡፡

13. .መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል፡፡

14. ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ ቢፈልጉ በአማራ ክልል ማረሚያ ቤት  ኮሚሽን  ቢሮ ቁጥር 11  ደረስ በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 60 35 በመደወል  መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአማራ ክልል ማረሚያ ቤት  ኮሚሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-05-05
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30
  • Bid opening: 2026-05-05 10:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: ANRS Prison Administration Commission
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 1,500.00 ብር
  • Published: Apr 20, 2026
  • Posted at: 2026-04-21T10:27:34.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders