የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን /አሚኮ/ የተለያዩ ዕቃዎችን እና አገልግሎቶችን መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 18/2018
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን /አሚኮ/
- ሎት 1. በድጋሜ የወጣ የሰቆጣ ኤፍኤም ጣቢያ የፈርኒቸር እና አካስቲክ ሥራ፣
- ሎት 2. የሰራተኞች የህክምና አገልግሎት፣
- ሎት 3. የሴቶች የዉበት ሳሎን.
- ሎት 4. የወንዶች የዉበት ሳሎን፣
- ሎት 5. የእጥበት /ላዉንደሪ/ አገልግሎት ፈቃድ ያላቸዉን በግልጽ ጨረታ ተጯራቾችን አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታዉ ለመወዳደር የሚፈለጉ ድርጅቶች፡-
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት፣ ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጠቅላላ ድምር ዋጋ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
3. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመግዛት አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 106 መዉሰድ ይችላሉ፡፡ ሰነዶችን በመሙላት ኮፒ በማድረግ በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት ለዚህ ሲባል በተዘጋጄዉ የጨረታ ሣጥን በ16ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
4. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
5. የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ (ስፒኦ)፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
6. ጨረታው የሚከፈትበት በ16ኛው ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፡፡ የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፡፡
7. ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
8. የሚፈለጉትን የፈርኒቸርና አካስቲክ ስራ፣ የሰራተኞችን የህክምና አገልግሎት፣ የሴቶች የዉበት ሳሎን፣ የወንዶች የዉበት ሳዉሎን፣ የእጥበት /ላዉንደሪ/ ዓይነት ብዛትና ስፔስፊኬሽን እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
9. የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደዉ አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 /09 18 70 74 85 /09 18 70 67 38 ደውሎ መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
ባህር ዳር
Tender details
- Deadline: 2026-05-05
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00
- Bid opening: 2026-05-05 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Amhara Media Corporation
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Apr 20, 2026
- Posted at: 2026-04-21T10:29:35.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.