በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ፅ/ቤት መድሃኒትና አላቂና ቋሚ የህክምና እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ግዥ መለያ ቁጥር የቀ/ጤ/ጣ 03/2018 ዓ.ም
በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ፅ/ቤት የቀበና ጤና ጣቢያ የፋይናንስና ግዥ አስተዳደር በጨረታ ቁጥር ቀ/ጤ/ጣቢያ 3/2018 በጀት ዓመት ለጤና ጣቢያው አገልግሎት እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 መድሃኒትና አላቂና ቋሚ የህክምና እቃዎች
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ቫት ተመዝጋቢ የሆነ የዘመኑን ግብር የከፈለበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስተር በአቅራቢነት የተመዘገቡና የአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና ቲን ነምበር ያላቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቀበና ጤና ጣቢያ ፋይናንስ ክፍል ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ዕቃ ጠቅላላ 6,000.00 ስድስት ሺህ ብር / በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራቾች ሰነዱን ለማስገባት በሚመጡበት ጊዜ ሳምፕል ለሚያሥፈልጋቸው ዕቃዎች ሳምፕል አብሮ ማስገባት አለባቸው። ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን ከሲፒኦ ጋር በአንድ ፖስታ ኮፒ ስነድ በሌላ ፖስታ አሽገው የድርጅቱን ማህተብ በማድረግና በፊርማ በማረጋገጥ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 –6፡00 ሰዓት እንዲሁም 7፡30 -11፡00 ሰዓት ድረስ የጤና ጣቢያው የግ/ን/አስ/ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታው ሳጥን በ11ኛ የሥራ ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአራዳ ክ/ከተማ በቀበና ጤና ጣቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የአንዱ ዋጋም ሆነ ጠቅላላ ዋጋ ሲቀመጥ ቫት አካቶ መሆን አለበት።
- ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራቾች በተመዘገቡበት ንግድ ፍቃድ ዘርፉ ብቻ መወዳደር አለባቸው።
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ ውል ከተፈራረመበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀን ውስጥ እስከ ጤና ጣቢያው ንብረት ክፍል በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብ ይኖርበታል። በዚህ አንቀጽ በተገለፀው መሰረተ ዕቃዋቹን ያላስገባ ካሸነፈበት ጠቅላላ ብር ላይ በየእለቱ 0.01 ተቀናሽ እንደሚደረግ አናሳስባለን።
- የገዙትን የጨረታ ሰነድኦርጅናልና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዎል።
- ከገዙት የጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልቶ የመጣ ማንኛውም ሰነድ ተቀባይነት የለውም። ጤና ጣቢያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ፡አድራሻ ቀበና ሼል የኦሮሚያ ደን ልማት ህንፃ ገባ ብሎ ቀበና መድሀኒዓለም ቤተከርስቲያን አጠገብ ነው።
ስልክ ቁጥር፡-011 811 2155 / 011 123 5607 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ፅ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-01
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): የጨረታው ሳጥን በ11ኛ የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-01 10:30
- Bid opening (note): የጨረታው ሳጥን በ11ኛ የሥራ ቀን 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ፅ/ቤት
- Bid bond: 6,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Apr 21, 2026
- Posted at: 2026-04-21T10:52:06.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.