የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ በካፒታል በጀት የባዮ ጋዝ የዶም ፓይፕ እና የባዮ ጋዝ ምድጃ /stove/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ፡- 009/2018
የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ በካፒታል በጀት የባዮ ባዝ የዶም ፓይፕ እና የባዮ ጋዝ ምድጃ /stove/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርት የምታሟሉ ሁሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው መሆን አለባቸው።
- የግዥውመጠን በየንግድ ዘርፉ 200,000/ሁለት መቶ ሺህ/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ 140,000 /አንድ መቶ አርባ ሽህ ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ መይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፣
- በጨረታው ፍላጎት ያላቸው ህጋዊ ድርጅቶች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 23 በመቅረብ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚቻል ሲሆን ተጫራቾች ለመወዳደር የመወዳደሪያ ሰነዶችን ሲመልሱ የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም፤ ፊርማ እና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቴክኒካልና ፋይናንሽያል በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን 8፡ዐዐ ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል። ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው በተመሳሳይ ስዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፤ ሆኖም የተወሰደው እርምጃ በማስረጃ የተደገፈ መሆን አለበት።
- የማቅረቢያ ጊዜ ውል ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ25 ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ርክክብ የሚፈፅም ይሆናል። ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፤
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 058 222 0132/ 058 220 1087 ዘወትር በስራ ቀናት መጠየቅ ይችላሉ።
- አድራሻ የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ቀበሌ ዐ7 ባህር ዳር ዩንቨርስቲ ዊዝደም ፊት ለፊት
አብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ
ባህርዳር
Tender details
- Deadline: 2026-05-06
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-06 14:30
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Amhara National Regional State Water and Energy Bureau
- Bid bond: 140,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Apr 21, 2026
- Posted at: 2026-04-21T11:11:55.000Z
Documents
Categories
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsKitchen EquipmentBuilding and Finishing MaterialsConstruction and Water WorksWater Pipes and FittingsSteel Raw Materials and ProductsSteel, Metals and AluminiumOther MetalsMetal and Metal WorkingAmharic2merkatoAmhara National Regional State Water and Energy BureauAmhara
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.