የአገው ግምጃ ቤት ከተማ አስተዳዳር ገንዘብ ጽ/ቤት ጠረጴዛ እና ወንበር ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ካላቸው ተጫራቾች መካከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአገው ግምጃ ቤት ከተማ አስተዳዳር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ
- ጠረጴዛ እና ወንበር
ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ካላቸው ተጫራቾች መካከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማረጋገጫ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ቅድመ ግብር ተቀናሽ 3 በመቶ ከአሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ ላይ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋና እና ቅጂ በማድረግ ከመጫረቻ ሠነዱ ጋር አያይዞ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ሲሞላ ያለምንም ስርዝ ድልዝ መሞላት አለበት፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ቀን ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ሚያዚያ 12/2018 ዓ.ም ጀምሮ በወጣው ግልጽ ጨረታ ለ21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ግዥ ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡\
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን እስከ ግንቦት 02/2018 ዓ/ም ድረስ የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) በመግዛት የጨረታ ሰነዱን ግዥ ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግዥ ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ግንቦት 03/2018 ዓም 3፡00 ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥ ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 በቀን ግንቦት 03/2018 ዓም 3፡00 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የህዝብ በዓል እና እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ የሚችሉ እና በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ ጥቃቅን ጽ/ቤት የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ ውል በሚይዝበት ወቅት ማስያዝ ወይም በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ ስራና ስልጠና ጽ/ቤት የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለበት፡፡
- አሸናፊ ድርጅት የሚሰራቸውን ጠረጴዛ እና ወንበር ስራዎች ማንኛውንም ማቴሪያሎች ወጭ በራሱ አቅርቦ መስራት የሚችል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበ ነው፡፡
- የውድድሩ ሁኔታ በሎት ዋጋ ይሆናል፡፡ በተጨማሪ በአብክመ የግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- የውል ማስከበሪያው ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ ውሉ ከሚጠናቀቅበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 30 ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት ቅድመ ክፍያ መውሰድ የሚችለው ለሚወስደው ቅድመ ክፍያ ተመጣጣኝ የሆነ መያዣ ወይም ኮላተራል ማስያዝ የሚችል፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ የአገው ግምጃ ቤት ከተማ አስተዳዳር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 224 07 24 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአገው ግምጃ ቤት ከተማ አስተዳዳር ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-11
- Bid closing time: 09:00
- Bid opening: 2026-05-11 10:00
- Region: Amhara
- Publishing entity: የአገው ግምጃ ቤት ከተማ አስተዳዳር ገንዘብ ጽ/ቤት
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Apr 20, 2026
- Posted at: 2026-04-21T11:56:56.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.