Accounting and Auditing, Accounting System Design
ሳፋሪኮም ቴሌኮሙኒኬሽንስ ኢትዮጵያ ኃ.የተ.የግ.ማ. የታወር ኦዲት፣ የመዋቅር ትንተና፣ ማጠናከርና የጥገና አገልግሎት አቅራቢዎች ይፈልጋል
Description
ፍላጎትን ማሳወቂያ የታወር ኦዲት፣ የመዋቅር ትንተና፣ ማጠናከርና የጥገና አገልግሎት I. መግቢያና እና መነሻ ሀሳብ ሳፋሪኮም ቴሌኮሙኒኬሽንስ ኢትዮጵያ ኃ.የተ.የግ.ማ የሚገነባቸው የቴሌኮሙኒኬሽን ማማዎች ለረዥም ጊዜ የሚያገለግሉ አስተማማኝ ፣ ደህንነት የተጠበቀና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ የታወር ማኔጅመንት ሲስተምን (TMS) በመተግበር ላይ ይገኛል። የዚህ እቅድ አንድ አካል በመሆን፣ ሳፋሪኮም በነባር የቴሌኮሙኒኬሽን ማማዎች ላይ ግምገማ ፣ የመዋቅርምዘና፣ የምህንድስና ትንተና ፣ የጥገና ስራዎች ማጠናከሪያዎችን ለማከናወን ብቃቱና ከፍተኛ ልምዱ ያላቸውን የግብአት አቅራቢዎች ለማሳተፍ አስቧል። ይህ ፍላጎት ያላቸውን ተሳታፊዎች ለማካተት የተሰጠ መግለጫ (EOI) በቴሌኮም የማማ ግንባታ የምህንድስና ዘርፉ ላይ አስተማማኝና ብቃት ያላቸውን አቅራቢዎች ለመለየት ያለመ ነው። ከታች ዋና ዋና ዝርዝር መስፈርቶች ያካተተ የጨረታ መጠየቃ (RFP) ለተጫራቾች ተጋርቷል። II. ፍላጎትን ማሳወቂያ ግባቶችን ለማቅረብ ፍላጎት ያላቸው አቅራቢዎች ከዚህ በታ የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች ስለመስጠታቸው የብቃት ማረጋገጫ ማሳየት አለባቸው።
- የማማዎች ምዘናና ምርመራ
- የማማዎቹ አወቃቀር ፣ የመሰረት ጥንካሬና እና በማማው ላይ የተገጠሙ መሣሪያዎችን ዝርዝር ምርመራ
- ዝርዝር የምርመራ መረጃዎች፣ የምህንድስና መመዘኛዎችንና የምስል ማስረጃዎች ጥንቅር።
- የተደረጉ የምርመራ ውጤቶችን ዲጂታል በሆነ መንገድ በማቅረብ በሳፋሪኮም የታወር አስተዳደር ሲስተም በኩል ማስገባት።
- የምህንድስና ምዘና
- ዝርዝር የኢዲት ሪፖርት ማደራጀት
- ተቀባይነት ያለው የታወር ትንተና ሶፍትዌር በመጠቀም መዋቅራዊ ትንተና ማቅርብ።
- ሙያዊ የምህንድስና ምክረ ሃሳቦችንና የጥገና ሙሉ እቅዶችን ማዘጋጀት።
- እንደ አስፈላጊነቱ የማጠናከሪያ ዘዴዎችን ማዘጋጀት።
- ማማዎችን የማጠናከርና ጥገና ስራ
- የማማዎች መሠረትን የማጠናከር ስራዎችን አፈፃፀም
- እያንዳዱን የማማ ክፍሎችን በሌላ ተለዋጭ ዕቃዎችን በመተካት መጠገን።
- ዝገት ካለ ማረምና እንዳይከሰት የቅድሚያ ጥንቃቄ እርምጃዎችን መውሰደ ።
- በቴሌኮሙኒኬሽን የማማዎች ግንባታ ወቅት ቅድሚያ ደህንነትን ያስቀደመ አፈጻጸም መከተል ።
- ዋነኛ የአቅራቢዎች (ተጫራቾች) መሠረታዊ መመዘኛ መስፈርቶች።
| መስፈርቶች | መገለጫዎች |
| ህጋዊ ማንነት፤ ለሁሉም የተጫራች ሰነዶች | ሁሉም አቅራቢዎች ህጋዊ የሆነ ምዝገባ ያስፈልጋቸዋል ። (ህጋዊ የምዝገባ የምስክር ወረቀት) |
| ተፈላጊ ብቃት | ሁሉም ተጫራች ከዚህ በፊት በማንኛውም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ወይንም የዓለም ባንክ ወይም በማንኛውም የዓለም አቀፍ ተቋማት እግድ ተጥሎበት በተመሳሳይ ውድድሮች ላይ እንዳይሳተፍ ያልተከለከለ፣ ወይም ብቁ ያልሆነ ተብሎ ያልተፈረጀ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት። |
| የተጫራችነት የምስክር ወረቀቶች | ተጫራቾች ህጋዊ የሆነ በኢትዮጵያ የንግድ ሚኒስቴር የምዝገባ ሂደት ውስጥ በማለፍ የተረጋገጥ ሀገር በቀል ድርጅት መሆኑን የሚያሳይ መሆን ይገባዎል። ከሀገር ውስጥ ተቋም ጋር በትብብር የሚሰራ የውጭ ሀገር አቅራቢ ከሆነ፣ ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ (ኢአይኤ) ሰነዶችን በማስገባት ከኢአይኤ የተሰጠ የንግድ ፈቃድና የኢንቨስትመንት ፈቃድ ማግኘት አለባቸው። (የምስክር ወረቀት ካለ ቅጂውን ማቅረብ ያስፈልጋል)ተጫራቹ ከአገር ውስጥ አጋሩ ጋር በጋራ ለመስራት የተሰማምበትን (JV) ሊያቀርብ ይገባል። |
| የሁሉም ተጫራቾች ሰነዶች ! | ▪ የተጫራቾች የድርጅት መግለጫ ለተፈልገው አገልግሎት በሚሆን መንገድ ከ25 ገፅ ባልበለጠ መቅረብ አለበት ▪ የንግድና ምዝገባ እና /ወይንም የመመስረቻ ሰነድ ▪ ወቅታዊ የግብር ከፋይነትን የሚያረጋግጥ ከሚመለከተው የታክስና ግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን የተሰጠ የግብር ምዝገባ/ክፍያ የምስክር ወረቀት፣ ወይንም በልዩነት እንደዚህ አይነት ልዩ መብት የሚያገኝ ከሆነ የግብር ነፃነት የምስክር ወረቀት። ▪ አስፈላጊ ከሆነ የንግድ ስም ምዝገባ ሰነድ ፤ ▪ የቫት ተመዝጋቢነት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ▪ እንደአስፈላጊነቱ የጥራት ማረጋገጫ (ለምሳሌ ISO፣ ወዘተ) እና/ወይም ከአቅራቢ ተቋማት የተሰጡ ሌሎች ተመሳሳይ የምስክር ወረቀቶች፣ እውቅናዎች፣ ሽልማቶች፣ ምስጋናዎች እና የብቃት ማረጋገጫ ሰነዶች ▪ የአካባቢ ጥበቃ ለማረጋገጥ መቻሉን የሚያሳዩ የምስክር ወረቀቶች፣ እውቅናዎች (ለምሳሌ ISO 14001, 14064) እና በንግድ ስራዎቹ ውስጥ ዘላቂ እና ጉዳት የማይስከትሉ ተፈጥሯዊ ኡደቱን የማያዛቡ ተጽእኖችን ለመቀነስ የሚረዱ አሰራሮች ሌሎች ማስረጃዎች። ▪ በኢትዮጵያ ውስጥ ለመስራት የተሰጠ ፈቃድ ▪ የJV፣ የኮንሰርቲየም ወይም የሽርክና ስምምነት፣ አቅራቢው በኢትዮጵያ ውስጥ ወይም ከአገር ውጭ ለሚገኝ ሌላ አካል ጋር በጋራ ለማስራት ያለውን ፍላጎት የሚያሳይ መገለጫ እያቀረበ ከሆነ። |
| ከዚህ በፊት የተሞከሩ ግን ያልተሳኩ ስራዎች | ተጫራቾች ባለፉት 5 ዓመታት ውስጥ ከገቡት የውል ስምምነቶች መካከል ያልተሳኩ ካሉ እንዲገልጽ። |
| ከፍርድ ቤት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች | ተጫራቾች ባለፉት 3 ዓመታት ውስጥ በተለያዩ ጉዳዮች የፍርድ ቤት ክሶች/ክርኮሮች ከነበሩባቸው ብይኖቹን ያሳውቃሉ ። |
| ከዚህ በፊት የነበሩ ተሞክሮዎች |
• የልምድ እና የእውቀት መስፈርቶች፡
ተጫራቾች ባለፉት አምስት (5) ዓመታት ውስጥ በቴሌኮሙኒኬሽን ማማ ኦዲት ፣ መዋቅራዊ ትንተና ፣ ወይም የማጠናከሪያ ፕሮጀክቶች ውስጥ ስለነበራቸው የስኬታማ አፈፃፀም/ልምድ የተሰጠ የእውቅና ማሳያ ሰርተፍኬቶችን በማያያዝ ማስረዳት አለባቸው ።
|
| የፋይናንስ ተደራሽነት | ተጫራቹ ሶስት (3) ዓመታትን ወደ ኃላ በመመለስ የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርቶችን ማቅረብ አለበት። |
| (በJV/ኮንሰርቲየም/ የሚሳተፉ ማህበራት በሙሉ ይህንን መስፈርት በጋራ ማሟላት አለባቸው።) | |
የብቁ ድርጅቶች ፍላጎቶችን ማሳወቂያ የመጨረሻ ቀን: ዓርብ, መስከረም 29, 2019 IV. የቴክኒክ መስፈርቶች ፍላጎት ያላቸው ማንኛውን ተጫራች ከላይ በተዘረዘሩት ዝርዝር መሰረታዊ መስፈርቶች መሰረት በማደርግ ሰነዶቻቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል ። V. ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ምላሾችን ማቅረብ በጨራታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ፍላጎት ተጫራቾች የፍላጎት መግለጫውን (EOI) በሶፍት ኮፒበማሸጋጀት [email protected] ይህ የጨረታ በይፋ ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባቸው። VI. ቀጣይ እርምጃዎች
- የቀረቡትን የፍላጎት መግለጫዎች (EOI) መገምገም
- የመጀመሪያውን ቅድመ ሁኔታ ያሟሉ ተጫራቾችን መለየት
- የፕሮፖዛል ጥያቄ (RFP) ማውጣት።
- ቴክኒካዊ እና የንግድ ግምገማዎችን ማካሄድ
- ለአሸናፊው ተጫራች የውል ማዘጋጀት።
ማስታወሻ
- ቅድመ ምዘናውን ያለፉ ተጫራቾች ብቻ ወደ ቀጣይ የRFP ሂደት ይሸጋገራሉ።
- ምንም ዓይነት የዋጋ ተመን በዚህ የፍላጎት መግለጫ (EOI) ጋር ተያይዞ መቅረብ የለበትም።
- ሳፋሪኮም ቴሌኮሚኒኬሽን ኢትዮጵያ ለዚህ የፍላጎት መግለጫ (EOI) ከቀረቡ ፕሮፖዛሎች የመምረጥ ወይም ሙሉ በሙሉ የመሻር መብቱ የተጠበቀ ነው። ማንኛውም እንደዚህ አይነት ውሳኔዎች የመጨረሻ ይሆናሉ ፤ በመሆኑም የአሰራሩን ውጤት ለተጫራቾች ከማሳወቅ ውጭ ምንም አይነት ግንኙነት አይደርግም።
- ተጫራቾት ይህንን ፍላጎት መግለጫውን (EOI) አዘጋጅቶ ለማቅረብ የሚያወጡትን ማንኛውንም ወጪዎች በራሱ ይሸፈናሉ።
Tender details
- Deadline: 2026-10-09
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-10-09 17:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Safaricom Ethiopia
- Buyer TIN: 0073915295
- Published on: 2merkato.com (Sep 26, 2026)
- Posted at: 2026-09-26T06:53:19.000Z
- Source: 2merkato