Accounting and Auditing, Accounting System Design
ተስፋ ድርጅት እ.ኤ.አ.የ2024 እና 2025 የበጀት ዓመት ያለውን የፕሮጀክቶቹን የሂሳብ መግለጫዎች ለመመርመር ብቁ ኦዲተሮችን አጫርቶ ለማሰራት ይፈልጋል
Description
የምርመራ (Investigative) ኦዲት አገልግሎት ጨረታ ማስታወቂያ
ተስፋ ድርጅት በሲቭል ማህበራት ኤጄንሲ በመዝገብ ቁጥር 0452 የተመዘገበ ሀገር በቀል መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን፤ በሀገራችን በተለያዩ ክልሎች ማለትም በጋምቤላ፣ በቤንሻንጉል፣ በኦሮሚያ፣ በአማራና በሲዳማ ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ ባሉት ቅርንጫፎች በትምህርት፣ በሙያ ሥልጠና እና በተለያዩ የልማት ሥራዎች የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ወገኖች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
ድርጅቱ እ.ኤ.አ.የ2024 እና 2025 የበጀት ዓመት ያለውን የፕሮጀክቶቹን የሂሳብ መግለጫዎች ለመመርመር ብቁ ኦዲተሮችን አጫርቶ ለማሰራት ይፈልጋል።
I. የሥራ ወሰን፤
- እ.ኤ.አ.የ2024 የበጀት ዓመት ከጃንዋሪ 1 እስከ ዲሴምበር 31/2024 እና
- እ.ኤ.አ የ2025 የበጀት ዓመት ከጃንዋሪ 1 እስከ ዲሴምበር 31/2025
II. ብቁነት እና ቴክኒካዊ መስፈርቶች፤
ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ድርጅቶች የሚከተሉትን ሰነዶች ከቴክኒካል ፕሮፖዛላቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡-
1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ከሂሳብ ቦርዱ የሚሰጥ ህጋዊ የምዝገባ የምስክር ወረቀት።
2. ትክክለኛ የቲን እና የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት።
3, በመንግሥታዊ/መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ኦዲት በማካሄድ ልምድ ያላቸው።
4. ተዛማጅ የሙያ ማረጋገጫዎችን (CPA/ACCA) እና ቢያንስ በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ የባችለር ዲግሪ ያላቸው የኦዲት ባለሙያዎች CV።
5. የቅርብ ጊዜ በመንግስታዊ/መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የኦዲት ስራ የሰሩበት የምስክርነት ደብዳቤዎች ያላቸው ቢሆኑ ተመራጭ ይሆናሉ።
6. የቴክኒክ እና የፋይናንስ ፕሮፖዛሎችን አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ኮፒ ማያያዝ።
7. እያንዳንዱ ተጫራች የሚያቀርበውን ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ብቻ በድርጅቱ ስም አሰርቶ እስከ ሕዳር 11/2019 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ከቴክኒካል (የህጋዊነት) ሰነዱ ውስጥ አብረው ማስገባት ይኖርበታል፡፡ ከሚያቀርበው ጥቅል ዋጋ 2% በታች /CPO/ የሚያቀርብ ለውድድሩ ብቁ አያደርግም።
ተጫራቾች የሚያስገቧቸውን የዋጋ ሰነዶች ቴክኒካል ሰነድ (ህጋዊነት) እና ቴክኒካል ፕሮፖዛል እንዲሁም ፋይናንሽያል ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) ከዚያም ሁለቱ የታሸጉ ኤንቨሎፖች በአንድ ትልቅ የታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 11/2019 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባችኋል።
ተወዳዳሪዎች ስለጨረታው አፈፃጸም የተዘጋጀውን ዝርዝር መግለጫ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) አየር ጤና ከሚገኘው ዋናው ቢሮ በመግዛት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሞልተው ሊያስገቡ ይችላሉ።
ጨረታው የጨረታው ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሕዳር 14/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡ ተስፋ ድርጅት ዋናው መ/ቤት አየር ጤና፣ሳሚ ካፌ ፊት ለፊት
የመ.ሳጥን ቁጥር 30153
ኢሜይል [email protected]
ስልክ ቁጥር 0113 694 480 / 0113 693 871
አዲስ አበባ
ተስፋ ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-11-20
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-11-23 14:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Hope Enterprise
- Buyer's registered address: አየር ጤና ሳሚ ካፌ ፊት ለፊት
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 400.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Nov 11, 2026)
- Posted at: 2026-11-11T10:29:36.000Z
- Source: Qelal Tenders