Accounting and Auditing, Accounting System Design
ቡሉኮ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር ከ2018 በጀት ዓመት ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ የበጀት ዓመታት የሂሳብ መርማሪ (ኦዲተር) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በግዥ መለያ ቁጥር
(ብ.ግ.ጨ.ቁ BTSC/NCB/Serv/05/2019)
ቡሉኮ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና በግል ባለሃብቶች ሽርክና የተቋቋመ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የልማት ድርጅት ነው። ድርጅታችን ከ2018 በጀት ዓመት ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ (እ.ኢ.አ የ2018፣ የ2019 እና የ2020) የበጀት ዓመታት የሂሳብ መርማሪ (ኦዲተር) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመግባት ለማሠራት ይፈልጋል። በዚህም መሠረት በግልፅ ጨረታው ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መረጃዎች ማሟላትና ማቅረብ አለባቸው።
1. ከሚመለከተው አካል በዘርፉ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የወሰደና እና የታደሰ፤
2. የታደሰ ንግድ ፈቃድና የምዝገባ ምስክር ወረቅት፣
3. የግብር ከፋይ የምዝገባ ሠርተፍኬት፣
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሠርተፍኬት፣
5. በጨረታ ለመሳተፍ ግብር ነፃ ስለመሆን አግባብ ካለው የገቢዎች መ/ቤት ደብዳቤ፤
6. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ) በባንክ የተረጋገጠ በሲፒኦ ወይም የባንክ ያለገደብ ዋስትና (ጋራንቲ) ማቅረብ የሚችል፤
7. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል በሸገር ከተማ ፉሪ ክ/ከተማ (ኬንተሪ ወደ ቡታጅራ በሚወስደው መንገድ 1.3 ኪ/ሜ ላይ) በድርጅቱ ቅጥር ግቢ የግዥና አቅርቦት መምሪያ ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ስዓት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 እስከ 10፡30 ሰዓት ቅዳሜ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት መግዛት ይቻላል።
8. ጨረታው ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት 4፡30 ሰዓት ላይ በግልፅ ይከፈታል።
9. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0946-81-73-02 ደውለው መጠየቅ ይችላል።
10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
አድራሻ፡ ኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሸገር ከተማ፣ ፉሪ ክ/ከተማ (ከኬንትሪ ወደ ቡታጅራ መንገድ 1.3 ኪ.ሜ)
ቡሉኮ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-11-25
- Bid closing time: 10:15
- Bid opening: 2026-11-25 10:30
- Region: Oromia
- Publishing entity: Buluko Textile Share Company
- Buyer's registered address: ሸገር ከተማ፣ ፉሪ ክ/ከተማ (ከኬንትሪ ወደ ቡታጅራ መንገድ 1.3ኪ.ሜ) የቀድሞው አይካ አዲስ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ
- Bid bond: 20,000.00 ብር
- Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
- Published on: Addis Zemen (Nov 10, 2026)
- Posted at: 2026-11-10T08:28:22.000Z
- Source: Qelal Tenders