መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ.የተ. ሰርገኛ ጤፍ እና ነጭ በቆሎ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ለመጀመሪያና ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 15 በሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ.የተ.
- ሎት1. ሰርገኛ ጤፍ ብዛት ሶሰት ሺህ ለሁለተኛ ጊዜ፣
- ሎት2. ነጭ በቆሎ ብዛት አሰር ሺህ
ለመጀመሪያ ጊዜ በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ካላቸው አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (ዋስትና) ወይም ሲ.ፒ.ኦ. ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅረቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዳይሰበሰብባቸው ፍቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባችሁ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 350 ብር የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሁለተኛ ጊዜ የወጣው ለ7 ተከታታይ ቀናት ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣው ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 101 መግዛት ይቻላል፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሁለተኛ ጊዜ የወጣው ለ7 ተከታታይ ቀናት ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣው ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ሲሆን ለሁለተኛ ጊዜ የወጣው በ7ኛው ተከታታይ ቀናት በ8፡00 ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣው በ10ኛ ተከታታይ የሰራ ቀናት በ8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
- ቅዳሜ ለዩኒየኑ የስራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታው ተወዳዳሪዎች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
- የጨረታው አሸናፊ በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አሸናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
- አሸናፊው የአሸነፋበትን እቃ በፍትህ ውል ከተመረመረ (ከተመዘገብ) የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል፤ ወይም ይሸፍናል ሰብሉን ለማንሳት የሚያስፈልጉ ማንኛውም የወዛደር ማስጫኛ እና የማጓጓዣ ወጭዎችን አሸናፊው የሚሸፍን ይሆናል፡፡
- ሰብሉ ሚገኝበት ቦታ ባ/ዳር ከተማ ከዩኒየኑ መጋዝን የሚገኝ ሲሆን ጥራቱን በአካል በማየት መሙላት አለበት፡፡ ከሎቶች ውስጥ መጠኑን ቀንሶ መሙላት አይቻልም፡፡
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ በህ/ስ/ማ/ የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስ/ቁ 09 11 59 05 34 / 09 18 08 26 26 96 መጠየቅ ይቻላል፡፡
መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ.የተ.
Tender details
- Deadline: 2026-04-30
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-04-30 14:30
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Amhara
- Publishing entity: Merkeb Multipurpose Farmers’ Cooperative Union LTD
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 350.00 ብር
- Published: Apr 20, 2026
- Posted at: 2026-04-21T12:04:47.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.