የቤ/ጉ/ክ/መ/ገቢዎች ባለስልጣን በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውሉ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የቤ/ጉ/ክ/መ/ገቢዎች ባለስልጣን በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውሉ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፤ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች፡-

1/ በተሰማሩበት የስራ መስከ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የገንዘብ ሚኒስቴር/ የክልል ገ/ኢ/ል/ቢሮ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው እንዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችሉ።

2/ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን እና የውል ስምምነቱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከታተመበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ ቀናት ከስኞ እስከ አርብ ዘወትር በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ እስከ 6 ሰዓት በቤ/ጉ/ክ/መ/ገቢዎች ባለስልጣን የግ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቀርቦ መግዛት ይችላሉ።

3/ ተጫራቾች የጨረታ ዕቃ ዋጋ መሙላት ያለባቸው በመ/ቤታችን በተዘጋጀው በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ብቻ መሆን አለበት፣ የጨረታ ሰነዱ ላይም የድርጅቱን ማህተም ስማቸውን ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በግልጽ ማስፈር ይኖርባቸዋል።

4/ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።

5/ ተጫራቾች የሚሸጡበትን ዋጋ በፖስታ/በኢቨሎፕ/ በማሸግ ማስታወቂያው ከታተመበት ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በተቋሙ በመገኘት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መስገባት አለባቸው፤ ለሚወዳደሩትና ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ለእያንዳንዱ ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።

6/ ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ በ10፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ሆኖም ግን ተጫራቾች በራሳቸው ፍላጎት ባይገኙ የጨረታው የመክፈቻ ስነ-ስርዓት አይስተጓጎልም.

7/ ተጫራቾች በሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን በሙሉ ወይም በከፍል በመሙላት መወዳደር ይችላሉ።

8/ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር የተጣጣመ እና ቢያንስ አስከ ሁለት ወራት የሚፀና መሆን አለበት።

9/ ተጫራቾች ለውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው ዋጋ 2% ማስያዝ አለባቸው፤

10/ የጨረታው የመክፈቻ ቀናት በበዓላት እሁድ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፍልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፤ ሆኖም ተጫራቾች ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ አይሸፍንም።
  • ለበለጠ መረጃ በቤ/ጉ/ክ/መ/ገቢዎች ባለስልጣን የግ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ በስልክ ቁጥር፡- 09 12 62 27 45 / 09 91 28 77 99 / 09 01 65 59 40 ደውሎ ማግኘት ይችላሉ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ባለሥልጣን


Tender details

  • Deadline: 2026-05-01
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ በ10፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-02 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Beneshangul Gumuz
  • Publishing entity: Benishangul Gumuz Revenue Authority
  • Bid bond: 100,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Apr 22, 2026
  • Posted at: 2026-04-22T09:27:09.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders