የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በየእለቱ ከሚታረዱ ከዳልጋ ከብት የሚገኘውን እርጥብ ቆዳና ከበጎች እና የፍየሎች የሚገኘው እርጥብ ሌጦ፣ የስጋና አጥንት መኖ፣ የዳልጋ ከብት ቀንድ እና ለሳሙና መስሪያ ግብዓት የሚሆነውን የተነጠረ ሞራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የተረፈ ምርት ሽያጭ
ጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከግንቦት 01 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓም ለሚያመርተው በየእለቱ ከሚታረዱ ከዳልጋ ከብት የሚገኘውን እርጥብ ቆዳና ከበጎች እና የፍየሎች የሚገኘው እርጥብ ሌጦ፣ የስጋና አጥንት መኖ፣ የዳልጋ ከብት ቀንድ እና ለሳሙና መስሪያ ግብዓት የሚሆነውን የተነጠረ ሞራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች፡
- በመስኩ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ እና የግብር ከፋይ ስርተፍኬት ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ ማስረጃ ኮፒ ማያያዝ አለበት።
- የጨረታ ማስከበሪያን በተመለከተ ለዳልጋ ከብት የጨረታ ማስክበሪያን የሚሆን ለሦስት የጨረታ ጊዜ ለእያንዳንዱ ብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር) እና በወር ውስጥ ለሚገኝው የበግና ፍየል ሌጦ የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) የዳልጋ ከብት ቆዳ ጨረታ ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች የቅድመ ክፍያ ለ10 ቀናት ብር 4,000,000.00 (አራት ሚሊዮን ብር) እና የበግና ፍየል ሌጦ ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች የቅድመ ክፍያ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ወይም በሲ.ፒ.ኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርባታል።
- ለስጋና አጥንት መኖ ለሦስቱ የጨረታ ጊዜ ለእያንዳንዱ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ለዳልጋ ከብት ቀንድ የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) እና ለተነጠረ ሞራ ለሦስቱ የጨረታ ጊዜ ለእያንዳንዱ ብር 300,000.00 (ሦስት መቶ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ወይም በሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል።
- ጨረታውን ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች ለዳልጋ ከብት ቀንድ ምርቱን በሳምንት ሁለት ቀን እንዲሁም ለስጋና አጥንት መኖ ምርቱ በሚመረትበት በሳምንት ሦስት ቀን (ሰኞ ማክሰኞ እና ሐሙስ) እና ለተነጠረ ሞራ ምርቱ በተመረተበት ቀን ሙሉ በሙሉ የእጅ በእጅ ሽያጭ በማከናወን ማንሳት የሚችል መሆን አለበት።
- ምርቱን ለመግዛት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች በጨረታ መመሪያ ላይ በተገለፀው መሰረት ይሆናል።
- አሸናፊው የሚኖረው መብትና ግዴታዎች በውል ውስጥ የሚካተት ይሆናል።
- ከቆዳና ሌጦ ውጪ ላሉት ምርቶች የተዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ ማርኬቲንግ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይቻላል።
- ጨረታው ለዳልጋ ከብት ቆዳ እና ለበጎች እና ፍየሎች እርጥብ ሌጦ ሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓም፣ ለስጋና አጥንት መኖ ሚያዝያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ለዳልጋ ከብት ቀንድ ሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም እና ለተነጠረ ሞራ ሚያዝያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በተመሳሳይ ሰዓት 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 141 63978 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ:።
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-05-07
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-05-07 10:30
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa Abattoirs Enterprise
- Buyer TIN: 0000028921
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር ከቆዳና ሌጦ ውጪ ላሉት ምርቶች
- Published: Apr 22, 2026
- Posted at: 2026-04-22T11:12:08.000Z
- Buyer website: https://www.aaae.gov.et/en/
Documents
Categories
Animal FeedAgriculture and FarmingOther SalesSales, Disposals and ForeclosureRaw materialsDisposal SaleShoes and Other Leather ProductsTextile, Garment and LeatherProducts and ServicesRaw Materials and SuppliesPoultry, Bee and Animal HusbandryAmharic2merkatoAddis Ababa Abattoirs EnterpriseAddis Ababa
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.