የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የክልሉ ንብረት የሆነውን በክልሉ ገንዘብ ቢሮ ግቢ፣ በተለያዩ የዞን መአከሎች የተለያዩ ጋራጆች ውስጥና በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የሃራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር፡-አፋር ንብ ማስ/ግል/ ሃ/ጨ/ተሽ/13/08/2018

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የክልሉ ንብረት የሆነውን በክልሉ ገንዘብ ቢሮ ግቢ፣ በተለያዩ የዞን መአከሎች የተለያዩ ጋራጆች ውስጥና በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ለመመዝገብ ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ በ2018 ዓ.ም የታደሰ ሰነድ ወይም ናሽናል አይዲ [National ID] ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች ሲፒኦ አስገብተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 14 ቀናት ውስጥ ብቻ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ከሰኣት 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ተሽከርካሪዎቹን ከላይ በተጠቀሰው ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣

3. ተሽከርካሪው ቀደም ሲል ያልተከፈለ የቦሎ እና የጉምሩክ ቀረጥ ግብር ወጪ እንዲሁም የስም ዝውውር፣ እና ሌሎች ወጪዎች ካለበት ያለበት ሁነው ወጭ በገዥው ይሸፈናል፣

4. ተጫራቾች ለሚገዙት ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ 150,000ብር (አንድ መቶ ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ጨረታ ከመጀመሩ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል። የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከሰመራ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣

5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን፤ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በክልሉ ገንዘብ ቢሮ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።

6. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለክልሉ መንግስት ገቢ ይደረጋል።

7. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፈባቸውን ተሽከርካሪዎች ሙሉ ክፍያ ከፍሎ እስከሚወስድ ድረስ ለውል አተገባበር ዋስትና የሚሆን ያሻነፈበት ጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ (10%) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት።

8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ተሸከርካሪውን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፣

9. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 251-33 -366 6767 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣

10. አገልግሎቱ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት

ሰመራ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-08
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-08 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Afar
  • Publishing entity: Afar National Regional State Government Procurement and Property Disposal Service Agency
  • Bid bond: ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ 150,000 ብር (አንድ መቶ ሺ ብር)
  • Published: Apr 23, 2026
  • Posted at: 2026-04-23T08:54:19.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders