የመ/ሰ/ማ/ዋ/አስ/ም/ሪጅን ጽ/ቤት የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን በጨረታ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የመ/ሰ/ማ/ዋ/አስ/ም/ሪጅን ጽ/ቤት የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን በጨረታ መሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት ለጨረታ የቀረቡትን ያገለገሉ ንብረቶች አይነት ብዛት መነሻ ዋጋ ሴሎች መረጃዎች ከመደበኛ የጨረታ ሰነድ ጋር በሰንጠረዥ ያቀረበ ሲሆን

1. አስተዳደሩ ለሽያጭ ያቀረባቸውን ያገለገሉ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር እቃዎችን ያገለገሉ ተሽከርካሪ ወንበር፣ የእንጨት ወንበር፣ የእንጨት ጠረፔዛ፣ ልዩ ልዩ የብረት በሮች እና መስኮቶች፣ ኮምፒዩተር፣ ፕሪንተር፣ ፋይል ካቢኔት እና ልዩ ልዩ የመኪና እቃዎችን ለመግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ለዚሁ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 200.00/ ሁለት መቶ ብር / በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

2. ተጫራቾች የጨረታ ማቅረቢያውን ሞልተው ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ሰነዱን ማስገባታቸውን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል።

3. ለጨረታ የቀረቡት ያገለገሉ ንብረቶች የመነሻ ዋጋ በሰንጠረዡ በተዘረዘረው መሰረት ሲሆን ተጫራቹ ሊገዛ የሚፈለገውን ንብረቶች በመለየት የሚገዛበትን ዋጋ ለዚሁ በተዘጋጀው ማቅረቢያ ሰነድ በ 2 ቅጽ ሞልቶ ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ አለበት።

4. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ብር 2000.00 ( ሁለት ሺህ ብር ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከጨረታ መክፈቻው ቀን ቀደም ብሎ ማስያዝ ይኖርበታል።

5. የጨረታ ማቅረቢያ ሰነዱ በታሸገ ፖስታ በፖስታው ላይ የተጫራቹ ሙሉ ስም አደራሻ እና ፊርማ መግለጽ አለበት።

6. ለጨረታ ከላይ በተራ ቁጥር 4 በተመለከተው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ያላስያዘ ከጨረታው ይሰረዛል።

7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ10 ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ /ታሽጎ / 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ሆኖም ግን ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በአካል ባይገኙም ጨረታው በሰዓቱ ይከፈታል።

8. አስተዳደሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9. ተጨማሪ መረጃ ከተፈለገ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ መጠየቅ ይቻላል።

አድራሻ፡- ሐረር ከተማ ቀበሌ 14 ልዩ ስሙ ቦቴ

ስልክ ፡- 09 33 34 25 96 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።

የመንግሥት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት

ሐረር


Tender details

  • Deadline: 2026-05-05
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-05 14:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Hareri
  • Publishing entity: Public Servant's Social Security Administration East Bureau Office
  • Bid bond: 2,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Apr 25, 2026
  • Posted at: 2026-04-25T08:49:04.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders