በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ ያገለገሉ ንብረትነታቸው የአዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ የሆኑትን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችና መለዋወጫዎች፣ የፎርከሊፍት መለዋወጫ እቃዎች ብዛት የተለያየ እና የተለያዩ ያገለገሉ የልብስ ስፌት (የአልጋ አጎበር ስፌት) ማሽኖችና መለዋወጫዎችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ ያገለገሉ ንብረትነታቸው የአዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ የሆኑትንና ዝርዝር መግለጫቸው ከዚህ በታች የተሰጡትን ንብረቶች ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ ቁጥር APPF/SP/02/2018 አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

1. ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችና መለዋወጫዎች

2. የፎርከሊፍት መለዋወጫ እቃዎች ብዛት የተለያየ

3. የተለያዩ ያገለገሉ የልብስ ስፌት (የአልጋ አጎበር ስፌት) ማሽኖችና መለዋወጫዎች

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን በሟሟላት መወዳደር ይችላሉ።

1) ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣

2) ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፀውን ሰነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ አዳሚ ቱሉ ባለው የፋብሪከው ዋና መስሪያ ቤት ሽያጭ ቢሮ ወይም አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ጅቡቲ ኢምባሲ ፊትለፊት ከሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

3) ተጫራቾች ለንብረቶች የሚገዙትን የጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ (2%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4) ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን አዳሚ ቱሉ ፋብሪካ በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ።

5) ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶች በሰም በታሸገ ኢንሸሎፕ በማድረግ ለጨረታው የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በፍት ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

6) ጨረታው እስከ ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ለተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዳሚ ቱሉ ፀረ ተባይ ፋብሪካ ንግድ መምሪያ ቢሮ የሚከፈት ይሆናል፡፡ የጨረታ ሳጥን ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

7) በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ካሸነፉበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) የስራ ቀና ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ያስያዙት ገንዘብ ለፋብሪካው ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛሉ።

8) ፋብሪካው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

  • ለበለጠ መረጃ፡ አ.አ ማስተባበሪያ ስልክ ቁጥር 011 666 3567 አ/ቱሉ 046 441 9287፣ 0991 589 980 (ንግድ መምሪያ) 0991 659 651(ሽያጭ ብድን)

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዳሚ ቱሉ የፀረ- ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-06
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-05-06 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Chemical Industry Corporation
  • Buyer address: ቦሌ ሩዋንዳ ናሚቢያ/ጅቡቲ ኤምባሲ ፊት ለፊት
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Apr 25, 2026
  • Posted at: 2026-04-25T10:17:43.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders