አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን እና በሠንጠረዡ ውስጥ የተመለከተውን ተሽከርካሪ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 መሠረት ንብረቱ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
- ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀን እና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል።
- ንብረቱን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
- በጨረታው ተራ ቁጥር 2 እና 3 ስር ለተገለፁት ንብረቶች ብቻ በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
- የጨረታ ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፤ ወረዳ 7 ለገሀር በሚገኘው የእቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ህንፃ B ላይ በሚገኘው የፎርክሎዠር
- እና ዴት ሊቲጌሽን ዲቪዥን የጨረታ ክፍል ውስጥ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 515 1153 እና 011 515 0711 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የመያዣ ሰጪው ስም |
የሰሌዳ ቁጥር |
የተሽከርካሪው ዓይነት እና የተሰራበት ዘመን |
የተሸከርካሪው ሞዴል |
የሻንሲ ቁጥር |
የሞተር ቁጥር |
የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር |
ጨረታዉ የሚካሄድበት ቀን |
የምዝገባ ሰዓት |
የጨረታ ሰዓት
|
ጨረታው የወጣበት ጊዜ |
|
1 |
ወ/ት እስከዳር አድማሱ ካሳሁን |
ተበዳሪዋ
|
A.A-02-C34105 |
አውቶሞቢል፣ ቻይና-ቼሪ፤ 2022 |
JETOUR
|
LVUDB21B7PF023218 |
SQRF4J16AVNJ04589 |
4,247,100.00 |
ግንቦት 06 ቀን 2018 ዓ.ም
|
8:30-9:30 |
9፡30-10፡00 |
ለመጀመሪያ ጊዜ |
|
2 |
አቶ በርሄ ገ/ መድህን |
ተበዳሪው
|
ኢት-03-94526
|
ቻይና፤ ሲኖ ትራክ 371 የፈሳሽ ጭነት ማመላለሻ ቦቴ/እ.አ.አ 2016 GC |
ZZ1257S4341W
|
LZZ5BLSF5GW159302
|
WD615.47* 161007029117*
|
7,600,000.00 |
ግንቦት 07 ቀን 2018 ዓ.ም
|
4:30-5:30
|
5:30-6:00
|
በድጋሚ
|
|
3 |
አቶ በርሄ ገ/ መድህን |
ተበዳሪው
|
ኢት-03-29251
|
ኢትዮጵያ፣ የHH ኢንጂነሪንግ ስሪት የሆነ የፈሳሽ ጭነት ማመላለሻ ተሳቢ/ እ.አ.አ 2017 GC |
HHENG
|
EAECBCHHEHO000068
|
--- |
3,800,000.00
|
Tender details
- Deadline: 2026-05-15
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-05-15 12:00
- Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Bank of Abyssinia S.C.
- Buyer address: Addis Ababa Ethiopia
- Bid bond: 25%
- Published: Apr 26, 2026
- Posted at: 2026-04-27T09:13:27.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.