የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፡-ኢፕድ 019/2018
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም፣ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ።
- በሥራ ዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር / ምስከር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ታከስ ክሊራንስና በመንግሥት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸዉ።
- ዕጩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ግዥውን አስመልክቶ የተዘጋጀዉን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ፋይናንስና ግዥ ዳት ግዥ ቡድን በአካል በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት በመዉሰድ የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ ከቫት ጋር በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በ4 በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒዎቻቸዉን ለየብቻ በማቅረብ ጉዳዩን አስመልክቶ በተዘጋጀዉ በፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት ግዥ ቡድን በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/ቢድ ቦንድ/ ማስያዝ አለባቸው።
- ጨረታዉ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት 1ኛ ፎቅ በአቅርቦት መመርያ ይከፈታል። ሆኖም ግን የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 011 156 9869
ኢ.ሜይል procurement@press.et
አድራሻ አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፌት
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-05-11
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-11 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Press Agency
- Buyer address: አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 100.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published: Apr 26, 2026
- Posted at: 2026-04-27T09:51:33.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.