የሀድያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዞኑ ትምህርት መምሪያ የመጀመሪያ ደረጃና የ7ኛ እና የ8ኛ ክፍል የመማሪያ መጽሐፍት ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል
Description
ለሁለተኛ ዙር የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የሀድያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዞኑ ትምህርት መምሪያ የመጀመሪያ ደረጃና የ7ኛ እና የ8ኛ ክፍል የመማሪያ መጽሐፍት ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች፡-
1ኛ. በመስኩ የታደሰ ንግድ ፈቃድ
2ኛ. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር
3ኛ. የቫት ተመዝጋቢነት ሠርትፍኬት
4ኛ, የዕቃና አገልግሎት አቅራቢነት ሰርትፍኬት ያላቸው ድርጅቶች፡ በሀድያ ዞን ፋ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 17 በአካል በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል እንድትገዙና ተጨራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000/ አንድ መቶ ሺህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የጨረታ መወዳደሪያ መምሪያው ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታዎችን ኦርጅናልና ኮፒ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 17 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እንድታስገቡና ጨረታውም በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ4፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የእረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046 178 4281/ 046 555 2337 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት
የሀድያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-05-11
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-11 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Hadiya Zone Finance and Economic Development Bureau
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: Apr 26, 2026
- Posted at: 2026-04-27T10:30:36.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.