ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መሬት አስተዳደር እና ኢንቨስተመንት ቢሮ በክልሉ ባሉት ፈርጅ 4 ከተሞች ላይ የመሬት መረጃን ዘመናዊ ለማድረግ የሚረዳ የመሬት መቆጣጠሪያ ነጥቦች ወይም GCP ተከላ ሥራን በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተደራጁ ጥቃቅንና አንስተኛ ማህበራት ለማሰራት ህጋዊ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 003/2018

ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መሬት አስተዳደር እና ኢንቨስተመንት ቢሮ በክልሉ ባሉት ፈርጅ 4 ከተሞች ላይ የመሬት መረጃን ዘመናዊ ለማድረግ የሚረዳ የመሬት መቆጣጠሪያ ነጥቦች ወይም GCP ተከላ ሥራን በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተደራጁ ጥቃቅንና አንስተኛ ማህበራት ለማሰራት ከዚህ በታች በተመለከተዉ መሰረት ህጋዊ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት ፡-

  • ተጫራቾች በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተደራጁ ጥቃቅንና አንስተኛ ማህበራት የሆነ ድርጅት 2018 በጀት ዓመት ፍቃዳቸውን ያደሱና የዘመኑ ግብር የከፈሉ። የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ። አግባብነት ካለዉ መንግስት ተቋም (በፈዴራል እና በሲዳማ ክልል) የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸዉ።
  • አስፈላጊ የግንባታ ማቴሪያሎች፡ የስራ ማሣሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶች በግላቸዉ አቅርበዉ ግንባታዉን መስራትና ማጠናቀቅ አለባቸዉ።
  • በሲዳማ ብ/ክ/መ ውስጥ ፕሮጀክት ሰርተዉ ለማስረከብ ከአሰሪና ከሚመለከታቸዉ መስራያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተዉ በስራ ወቅት ከአሰሪ መ/ቤት ወይም ከአማካሪ መ/ቤት ማንኛዉም አይነት የስራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸዉ ኮንተራክተሮች የጨረታ ሰነድ መግዛት ሆነ መወዳደርም አይችሉም።
  • በገባዉ ውል መሰረት ፕሮጀክት ሰርቶ ያስረከበና የመልካም ስራ አፈፃፀም ማቀረብ የሚችሉ።
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ Cpo ማስያዝ የሚችሉ።
  • ጨረታዉ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ይዉላ።
  • ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀናት ውስጥ እስከ ቢሮ በመምጣት የማይመለስ 100 ብር በመክፈል መግዛት አለበት።
  • ድርጅቶቹ ለመወዳዳሪያ ያቀረቡ የብቃት ማረጋገጫ (ቴክኒክ) ሰነዶችዋና (ኦርጅናል) አቅርቦ መወዳዳር አለባቸዉ። ይህ ተጣርቶ ኮፒዉ ከዋናዉ ጋር ተመሳከሮ ትከክለኛ ካልሆነ ድርጅቱ ከውድድር ውጪ ይሆናል።
  • የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) ሁለት ሁለት ኮፒዎች እንዲሁም የቴክንካል አንድ ዋና (ኦርጅናል)ሁለት ሁለት ኮፒዎች ሰነድ በተለያየ ኢንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸዉ ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ዉስጥ ተከተዉና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 11ኛው ቀን ከጧት 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብ/ክ/መ/የመሬት አስተዳደር እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ግዥ/ፋ/አስተዳደር ክፍል ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  • ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸሁ በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰዉ ቀንና ቦታ 6፡30 ሰዓት ላይ ታሽገዉ 10፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መክፈት አያግደዉም።
  • 11ኛው ቀን በበዓል ወይም ከስራ ቀን ውጪ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸዉ ቦታና ሰዓት ይሆናል።
  • ቢሮ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል አከባቢ ሱሙዳ ፊት ለፊት ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 12 13 33 05 / 09 16 35 78 76 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመሬት አስተዳደርና ኢንቨስትመንት ቢሮ

ሀዋሳ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-06
  • Bid closing time: 12:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ6፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-06 16:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 10፡00 ሰዓት
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መሬት አስተዳደር እና ኢንቨስትመንት ቢሮ
  • Bid bond: 10,000.00 ብር
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Apr 26, 2026
  • Posted at: 2026-04-27T10:44:09.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders