በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ የወረዳ 5 ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ መድሃኒቶች እና ላብራቶሪ ሪኤጀንት በ3ኛ ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ የወረዳ 5 ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ መድሃኒቶች እና ላብላቶሪ ሪኤጀንት በ3ኛ ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
1) ሎት 1- የላብራቶሪ ሪኤጀንት
2) ሎት-2- መድሃኒቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦችን በጨረታው እንዲወዳደሩ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 ለተጠቀሱት ግዥዎች አግባብነት ያለው፤
1. ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና በዘርፉ የተሰማሩ፤
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤
3. ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር አቅራቢዎች ዝርዝር ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
4. የቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸው የሚገልጽ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
5. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
6. በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. ከመድሃኒትና ቁጥጥር ባለስልጣን የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
8. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር /10,000 / /አስር ሺህ / ብር ከህጋዊ ባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ ብቻ) ማስያዝ ይኖርበታል።
9. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 2- ብር /10,000/ /አስር ሺህ/ ብር ከህጋዊ ባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ ብቻ) ማስያዝ ይኖርበታል።
10. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ወረዳ 5 ጤና ጣቢያ የግ/ቡድን ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች ሎት 1 እና ሎት 2 የተጠቀሱትን መድሃኒቶችና ላብራቶሪ ሪኤጀንቶች የሚያቀርቡበትን ሰነድ የአንዱን ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በመግለፅ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በማድረግ በታሸገ ፖስታ ሙሉ አድራሻቸውንና የጨረታውን አይነት (ሎት) በመጥቀስ ወረዳ 5 ጤና ጣቢያ/የግ/ቡድን/አስ/የስራ ሂደት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
11. የጨረታውን ሂደት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን 3፡00 ታሽጎ በ3፡30 ሠዓት ላይ በወረዳ 5 ጤና ጣቢያ ሁለገብ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል። ተጫራቾች ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ።
12. አሸናፊ ተጫራቾች ዕቃውን ሲያስገቡ ከጠዋቱ 2:30 - 5፡30 ሰዓት ሲሆን ከሰዓት ከ7፡30 – 9፡30 ሰዓት ብቻ መሆኑን እያሳወቅን ከተጠቀሰው ሰዓት ውጪ የሚመጡትን የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን።
13. ከጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት በኋላ ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊ መሆኑን በደብዳቤ ከተገለጸለት በኋላ ከሰባት(7) የስራ ቀን በኋላ ቀርቦ ያሸነፈበትን የውል ማስከበሪያ 10% ህጋዊ ሲፒኦ በማስያዝ ውል መዋዋል ይኖርበታል። እቃዎቹን በተቋሙ ንብረት ክፍል ድረስ አጠናቀው ማቅረብ ግዴታ ነው።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 5 ጤና ጣቢያ ልዩ ስሙ ከኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያ ከፍ ብሎ (72 ሰባራ ድልድይ)
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011 369 7443
በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ የወረዳ 5 ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-05-08
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 3፡00 ሠዓት
- Bid opening: 2026-05-08 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ3፡30 ሠዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Kolfe Keranyo Sub City Woreda 5 Health Office
- Buyer address: ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 5 ጤና ጣቢያ ልዩ ስሙ ከኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያ ከፍ ብሎ (72 ሰባራ ድልድይ)
- Bid bond: 10,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: Apr 26, 2026
- Posted at: 2026-04-27T10:47:02.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.