ብርሃን ባንክ አ.ማ. ያገለገሉ ንብረቶች ለማንኛዉም ግለሰብ ወይም ድርጅት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁ. ብ/ባ/ፕ/ማ/ሎ - 09/18

ብርሃን ባንክ አማ ከዚህ በታች የተገለፁትን ያገለገሉ ንብረቶች ለማንኛዉም ግለሰብ ወይም ድርጅት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

..

ለጨረታ የቀረቡ ያገለገሉ ንብረቶች ዝርዝር

1

ያገለገሉ ዴስክቶፕ ኮምፕዩተሮች

2

ያገለገሉ የቢሮ ማሽኖች

3

ያገለገሉ የቢሮ ፈርኒቸሮች

4

ያገለገሉ የተሸከርካሪ ጎማ እና ባትሪዎች

5

ያገለገሉ ሌሎች እቃዎች

1. ተጨራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች፤ ዝርዝራቸዉ፣ ብዛታቸዉ፣ የጨረታ መነሻ ዋጋቸዉ ለጨረታዉ በተዘጋጀዉ ሰነድ በዝርዝር ተቀምጧል።

2. ለጨረታ የቀረቡት ያገለገሉ ንብረቶች ቃሊቲ ጉምሩክ ፊት ለፊት ባቡር ጣቢያ መጨረሻ በተለምዶ ሰማያዊ ሕንፃ ተብሎ የሚጠራዉ ሕንጻ ባለበት በኩል በስተቀኝ ባለዉ መንገድ ወደ ዉስጥ ገብተዉ የግብርና ምርት ማሳደጊያ አቅራቢ ድርጀት ሕንፃ አጠገብ በሚገኘዉ የባንኩ መጋዘን በመገኘት ማየት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በማንኛዉም የብርሃን ባንክ ቅርንጫፍ ክፍያ ፈፅመዉ ደረሰኙን በማቅረብ፣ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት የቀድሞዉ ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ወመሳድኮ ግቢ ዉስጥ 2ተኛ ፎቅ ከፕሮፐርቲ ማኔጅመንት እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር ቢሮ ለጨረታዉ የተዘጋጀዉን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች ሊገዙት ያሰቧቸዉን ያገለገሉ ንብረቶች ጠቅላላ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በብርሃን ባንክ ስም የተዘጋጀ C.P.O ማስያዝ ይኖርባቸዋ።

5. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ያገለገሉ፤ ዴስክቶፕ ኮምፕዩተሮች፣ የቢሮ ፈርኒቸሮች፣ የቢሮ ማሽኖች፣ የተሸከርካሪ ጎማ እና ባትሪዎች እና ሌሎች እቃዎችን ሊገዙ የሚችሉበትን ዋጋ በተዘጋጀዉ የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ በመሙላት ከጨረታ ማስከበሪያ C.P.O ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ግንቦት 05 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘዉ ወመሳድኮ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር ቢሮ ለጨረታዉ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።

6. ጨረታዉ ግንቦት 05 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘዉ ወመሳድኮ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል:: ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ባይገኙ በሌሉበት ይከፈታል።

7. ተጫራቾች ያሸነፉባቸዉን ያገለገሉ ንብረቶች ባቀረቡት ነጠላ ዋጋ መሰረት በአጠቃላይ ብዛቱ ተባዝቶ ጠቅላላ ዋጋዉን በመክፈል አሸናፊነታቸዉ በተገለፀላቸዉ በአስር ቀን ዉስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህን ሳያደርጉ ቢቀር ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።

8. ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ ሊሰርዝ ይችላል።

9. በስልክ ቁጥር 09 18 89 07 21 ወይም 011 443 7439 ወይም 011 663 1729 ደዉለዉ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።


Tender details

  • Deadline: 2026-05-13
  • Publishing entity: Berhan Bank S.C.
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Apr 26, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders