የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ (አ.ማ) ለረጅም ጊዜ ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ ዓይነት ቲዮታ ያሪስ አውቶሞቢሎች እና ሱዙኪ ሞተር ሳይክሎችን ባሉበት ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር FA-09/2025/26
የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ (አ.ማ) ለረጅም ጊዜ ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ ዓይነት ቲዮታ ያሪስ አውቶሞቢሎች እና ሱዙኪ ሞተር ሳይክሎችን ባሉበት ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ለመግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች የተቀመጠውን መመሪያ መከተል ይጠበቅበታል።
የጨረታ መመሪያ፦
1. የንብረቶቹን ዝርዝር ሁኔታ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከሚያዝያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ግንቦት 03 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነድ በአቅራቢያዎ ከሚገኝ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ቅርንጫፍ ሂሳብ ቁጥር EIB1446500010001 የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) ገቢ በማድረግና የጨረታውን ሰነድ ከባንኩ ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመውሰድ እና ንብረቱ በሚገኝበት ሸገር ከተማ ሱሉልታ በሚወስደው መነአቢቹ ክ/ከተማ ሚዛንን አለፍ ብሎ በቻይና ጋራጅ ወደ ቀኝ በሚያስገባዉ ቅያስ ከዋናዉ መንገድ 100 ሜትር ገባ ብሎ አነን ሰላሌ ተብሎ በሚታወቀው የባንኩ ግምጃ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በመገኘት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ብቻ በተቀመጠው ፕሮግራም መሠረት ሚያዝያ 26፣ 29 እና 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧቱ 3፡30 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት እንዲሁም በመዝጊያው እለት ግንቦት 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት መጎብኘት ይችላሉ።
2. ገዥዎች የሚገዙበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ጨረታ መዝጊያ ግንቦት 03 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ወረቀት እና የግብር ከፍያ ምዝገባ ሰርትፊኬት ወይም ካርድ ያላቸዉ ተጫራቾች ቦሌ መንገድ ራንግ ሪልስቴት ሕንፃ 7ኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል በአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በመላክ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በማስገባት መጫረት ይችላሉ።
3. ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከተገለጸበት ከሚያዝያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጨረታው መዝጊያ ግንቦት 03 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ ግንቦት 03 ቀን 2018 ዓ.ም በ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ጨረታው በዛው ዕለት 8፡30 ሰዓት ላይ ቦሌ መንገድ ራንግ ሪልስቴት ሕንፃ 7ኛ ፎቅ የፋሲሊቲዎች እና ንብረት አስተዳደር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል።
4. ተጫራቾች ለሚጫረቱበትን ንብረት /ጨረታ/ መነሻ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ስም በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. የጨረታው አሸናፊዎች ባሸነፉበት ንብረት ላይ የሚከፈሉ የቦሎ እና ከስም ዝውውር ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ይከፍላል፤
6. ተጨራች የሚገዛበት የመግዣ ዋጋ በግልጽ በዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በተቀመጠው መሠረት ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% መካተቱን ወይም አለመካተቱን ለይቶ መጻፍ ይኖርበታል፤ ነገር ግን አሻሚ ቦታ ላይ ወይም ሁለቱም ቦታ ላይ ተመሳሳይ ዋጋ ከጻፈ ምንም ካልተገለጸ ባንኩ የቀረበው ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተካቶ እንደቀረበ ታሳቢ ያደርጋል።
7. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱን የሚገልፅ ደብዳቤ ከባንኩ ከተቀበለበት ዕለት ጀምሮ ያሸነፈበትን አጠቃላይ ዋጋ በ 5 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ በመክፈል የሽያጭ ውል መፈጸም አለበት በእነዚህ ቀናት ውስጥ የሽያጩን ገንዘብ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።
8. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
9. ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ራንግ ሪል እስቴት ህንፃ 7ኛ ፎቅ የባንኩ ንብረት አስተዳደር ቢሮ
ስልክቁጥር፡- 011 557 6174
ፖ.ሳ.ቁ.16936 /አዲስ አበባ/
የኦሮሚያ ኀብረት ስራ ባንክ /አ.ማ/
ማህበረሰብን ማጎልበት፣ ህይወትን መለወጥ!
Tender details
- Deadline: 2026-05-11
- Publishing entity: Cooperative Bank of Oromia S.C.
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: Apr 26, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.