ኢስት አፍሪካን ላየን ብራንድስ ማኑፋክቸሪንግስ አ.ማ. በድርጅቱ ውስጥ ተከማችተዉ የሚገኙ ልዩ ልዩ አሮጌ የብረታ ብረት ስክራፖችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቅያ

ኢስት አፍሪካን ላየን ብራንድስ ማኑፋክቸሪንግስ አ.ማ በድርጅቱ ውስጥ ተከማችተዉ የሚገኙ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ልዩ ልዩ አሮጌ የብረታ ብረት ስክራፖችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የእቃ አይነቶች ዝርዝር

መጠን

1

የተለያዩ አሮጌ ብረታ ብረቶች

በምድር ሚዛን ተለክቶ በተገኘዉ

2

የተለያዩ ጋልቫናይዝድ ብረታ ብረቶች

በምድር ሚዛን ተለክቶ በተገኘዉ

3

የተለያዩ የተሰባበሩ የዲናሞ ብረቶች

በምድር ሚዛን ተለክቶ በተገኘዉ

ተጫራቾች ለጨረታዉ ማስከበርያ ሀምሳ ሺ ብር (50,000.00) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ የአካዉንት ስም ኢስት አፍሪካ ላየን ብራንድስ አ.ማ (East Africa Lion Brands Manufacturing SC) ገቢ አድርገዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡ የጨረታ ማስከበርያዉ ላሸናፊዉ ከሚገዛዉ እቃ ላይ ታሳቢ ሲደረግለት ለተሸናፊዉ ወድያዉ ይመለስለታል:: ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፍቃድና የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር( ቲን ሰርተፍኬት ) ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ድርጅቱ ያዘጋጀውን የዋጋ ማቅርቢያ ቅፅ በ500 (አምስት መቶ) ብር በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል:: የጨረታ ሳጥኑ ማክሰኞ ግንቦት 4 2018 ዓም ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 9፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢስት አፍሪካ ላየን ብራንድስ ማኒፋክቸሪንግ አክሲዮን ማህበር መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ በግልፅ ይከፈታል፤ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታውን በሚከፍትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም።

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ::

አድራሻ፡ ቢሾፍቱ ወረዳ ዲባዩ ቀበሌ ደካ ቦራ (ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ 0917013050/0953606560 መደወል ይችላሉ)


Tender details

  • Deadline: 2026-05-12
  • Publishing entity: East African Lion Brands Manufacturing Co.Ltd
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: Apr 26, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders