የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ተቋማት የሆኑ ያገለገሉ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ተቋማት የሆኑ ያገለገሉ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣ በስክራኘ መልክ የሚወገዱ ተሸከርካሪዎች፣ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ የተለያዩ ንብረቶች (

  • የተሽከርካሪ ጎማዎች፣
  • ባትሪዎች፣ 
  • ከነመዳሪዎች፣
  • ቸርኬዎች፣ ፍላፖች፣
  • የሬንጅ በርሜሎች ከነክዳናቸው፣
  • የህከምና እቃዎች፣
  • ጀኔሬተሮች ያገለገሉ አሳንሰርሊፍት/፣
  • የአገልግሎት ዘመናቸውን የጨረሱ ተጠግነው አገልግሎት የማይሰጡ የኮምፒውተርና ተያያዥነት ያላቸው የኤሌትሮኒክስ እቃዎች)

ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

  1. ተጫራቾች ከአፍንጮ በር ወደ 6 ኪሎ በሚወስደው መንገድ ፍቅር ፕላዛ ህንፃ ላይ በሚገኘው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመምጣት የተለያዩ ተቋማት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ በስክራኘ መልክ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎች እና ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ ለእያንዳንዳቸው ዝርዝርና ብዛት የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 600.00 (ስድስት መቶ ብር)፣እንዲሁም የተለያዩ የአገለገሉ ንብረቶች (የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ባትሪዎች፣ ቸርኬዎች፣ ፍላፖች፣ ከነመዳሪዎች፣ ያገለገሉ አሳንሰር /ሊፍት/ እና የተለያዩ የሬንጅ በርሜሎች ከነክዳናቸው ዝርዝርና ብዛት የያዘ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) እና የአገልግሎት ዘመናቸውን የጨረሱ ተጠግነው አገልግሎት የማይሰጡ የኮምፒውተርና ተያያዥነት ያላቸው የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ተገኝተው መግዛት ይችላሉ።
  2.  በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ስር ዋጋ በአሃዝ እንዲሁም በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገ ኤንቨሎፕ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 402 ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከ ሚታሸግበት ሰዓት ድረስ ተጫራቶች ሰነድን ማስገባት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች በአሃዝና በፊደል እንዲሁም በነጠላና በጥቅል በሰጡት ዋጋ መካከል ልዩነት ካለ አገልገሎቱ ከፍተኛውን ዋጋ ወስዶ ያወዳድራል።
  4. ተጫራቾች ትክክለኛ አድራሻቸውንና ስማቸውን በመግለጽ በመጫረቻ ሠነዳቸው ላይ መፈረም አለባቸው።
  5. ተጫራቶች በአንድ መለያ ቁጥር(መደብ) ስር ያለውን ንብረት ብዛት በሙሉ መጫረት አለባቸው።
  6.  ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጁትን የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ቸርኬዎች፣ ባትሪዎች፣ ፍላፖች፣ከነመዳሪዎች፣ የሬንጅ በርሜሎች ከነክዳናቸው፣ ጀኔረተሮች፣ የህክምና እቃዎች ፣ ያገለገሉ አሳንሰር /ሊፍት/፣ የአገልግሎት ዘመናቸውን የጨረሱ ተጠግነው አገልግሎት የማይሰጡ የኮምፒውተርና ተያያዥነት ያላቸው የኤሌክትሮኒከስ እቅዎች እና ሌሎችም የአንዱን መስሪያ ቤት በአይነት የተቀመጡትን በጥቅል መጫረት አለባቸው።
  7.  ተጫራቾች ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ድረስ በመሄድ ንብረቱን አይተው መጫረት ወይም ዋጋ መስጠት አለባቸው፡፡ነገር ግን ንብረቱን ሳያዩ ቢጫረቱና ቅሬታ ቢቀርብ አገልግሎቱ ሀላፊነቱን አይወስድም።
  8. ለሚገዙት የተለያዩ ተቋማት ተሽከርካሪዎችና በቁርጥራጭ መልክ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎች የጨረታ መነሻ ዋጋውን 20 በመቶ (20%)፣ ሌሎችን ንብረቶችን፣ ደግሞ የጨረታ መነሻ ዋጋውን 10 በመቶ (10%) እንዲሁም የአገልግሎት ዘመናቸውን የጨረሱ ተጠግነው አገልግሎት የማይሰጡ የኮምፒውተርና ተያያዥነት ያላቸው የኤሌክትሮኒክስ እቅዎች 100,000.00/አንድ መቶ ሺህ ብር የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ሲ.ፒ.ኦ. ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል።
  9. የአገልግሎት ዘመናቸውን የጨረሱ ተጠግነው አገልግሎት የማይሰጡ የኮምፒውተርና ተያያዥነት ያላቸው የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች አሸናፊ ተጫራች ከፍያውን በተመለከተ የጨረታ አሸናፊው ከአገልሎቱ ጋር በሚደረግ የውል ስምምነት መሰረት ይፈፀማል ፣ሆኖም የጨረታ አሸናፊው የውሉን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የሚያስይዙ ይሆናል።
  10.  የጨረታ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 504 ይከፈታል፡፡ ሆኖም የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል።
  11. ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉልም፡፡
  12.  አገልግሎት ዘመናቸውን የጨረሱ ተጠግነው አገልግሎት የማይሰጡ የኮምፒውተርና ተያዥነት ያላቸው የኤለትሮኒክስ እቅዎች ጨረታ ላይ የሚሳተፍ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ ከአካባቢ ጥበቃ የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ነጻ ሰርተፊኬት፤ በኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻ (E-WASTE) ማስወገድ ፈቃድ፤ የዘመኑን ግብር የከፈለበት የህጋዊነት ማረጋገጫ ያለው እና መልሶ መጠቀም (Recycle) የሚያደርግበት በቂ መጋዘን ማሽነሪና የሰዉ ሃይል ሊኖረው ይገባል።
  13. ተሽከርካሪዎች የነበረባቸው የቦሎ ዕዳ እና የስም ዝውውር ወጪ በአሸናፊ ተጫራቾች ይሸፈናል።
  14. አንድ ተጫራች አንድ ተሽከርካሪ እና ከአንድ የመ/ቤት ንብረቶች በላይ መግዛት ይችላል፡፡ ሆኖም አንድ ተጫራች ለአንድ ተሽከርካሪ፤ ለአንድ መደብ ንብረት የተለያየ ዋጋ በመስጠት መወዳደር አይችልም።
  15. በመነሻ ዋጋና በታች የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት የለውም።
  16. የጨረታ ሳጥን ከተዘጋ በኋላ ኮድ ወይም መለያ ቁጥር ሲጽፍ ተሳስቻለሁ ወይም ሳልጽፍ ቀርቻለሁ የሚሉ ጥያቄዎች ተቀባይነት የላቸውም።
  17. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለአገልግሎቱ ገቢ ይደረጋል፡፡
  18. ንብረቱን በ10የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው።
  19. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ ከጨረታው መውጣት ወይም የሰጠውን ዋጋ ማሻሻል ወይም መለወጥ አይችልም።
  20. የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚመጡ ማናቸውም ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-557-86-71 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡ አገልግሎቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-14
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-14 10:15
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡15 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa City Administration Public Procurement and Property Disposal Service
  • Buyer address: Mexico Sengatera, behind St. Mary University College, located at Yobek Commercial center.
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published: Apr 27, 2026
  • Posted at: 2026-04-28T07:26:17.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders