በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ ያገለገሉ ዕቃዎችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፦ አሸጨ /001 / ኦኩስፋ-2/2018 ዓ.ም
1. በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ በብሄራዊ ግለፅ ጨረታ ጥቅል (ሎት-1) ፡- ያገለገሉ የተለያዩ አሮጌ ጎማዎች፣ ጥቅል ( ሎት-2) ፡- ያገለገሉ አሮጌ ባርመሎች፣ ጥቅል ( ሎት 3) – ያገለገሉ የተለያዩ አሮጌ ባትሪዎች ፤ጥቅል (ሎት –4) ያገለገሉ አሮጌ ሞረዶች፣ ጥቅል ( ሎት- 5) - ያገለገሉ አሮጌ ብረት ድስቶች እና ጥቅል ( ሎት -6 ) -- ያገለገሉ የፕርንተር ቶነሮች አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የ120 ቀን የባንክ ሦስትና BID BOND/ በመስኩ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ተጫራቾች በመንግስት ግዥ የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር/supplier List/ ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና በተጨማሪ የበጀት ዓመቱን ታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
3. ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀን ውሎ በአስራ አንደኛ ቀን ይከፈታል። የጨረታውን መክፈቻ ትክክለኛ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።
4. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ስነድ ለሁሉም የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00፣ ከሰዓት በኃላ ከ7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00) ቀጥሎ በተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
5. የጨረታው ሰነድ የሚሸጥበት ለውድድር የቀረበ ሰነድ የሚገባበትና የሚከፈትበት አድራሻ ቀጥሎ በተመለከተው ነው፡-
5.1. ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ የስኳር ፋብሪካዎች ማስተባበሪያ ቢሮ ቶታል ሶስት ቁጥር ማዞሪያ 300 ሜትር ከፍ ብሎ ተዘነኦ ሆስፒታል አጠገብ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ።
ስልክ ቁጥር፡ 09-91-14-94-85 / 09 30 85 64 15 / 09 40 20 94 64
አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ
6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ሎት የማስከበሪያ ዋስትና ለእያናዳንዱ ብር 10.000.00 (አስር ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
7. የዕቃው ርክክብ የሚፈፀመው ኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ ነው።
8. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ነው።
9. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለ28 ቀናት ነው።
10. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ
Tel- 09 40 20 94 64
ኃይል ውሃ
አዲስ አበባ ግዥ ማስተባበሪያ ቢሮ
Tel: 09-91-14-94-85 / 09 30 85 64 15
አዲስ አበባ
በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ
Tender details
- Deadline: 2026-05-11
- Publishing entity: Ethiopian Sugar Industry Group
- Bid bond: 10,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: Apr 27, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.