በደቡብ ኢ/ክ/መንግሥት የጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት የኤለክትሮኒክስ ግዥ፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃ ግዥ፣ የመኪና ጥገና የሙያ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢ/ክ/መንግሥት የጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት፡-
- የኤለክትሮኒክስ ግዥ
- የመኪና መለዋወጫ ዕቃ ግዥ
- የመኪና ጥገና የሙያ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ፦
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፤
3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር Tin No ያላቸው፣
4. የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤
5. የጨረታ ማስከበሪያ 40,000/አርባ ሺህ ብር/ ጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ የምችሉ፤
6. ለመኪና ጥገና የሙያ ግዥ በትራንስፖርትና መንገድ ልማት የተሰጠ ብቃት ማረጋገጫ ደረጃ 2 /ሁለት እና ከዚያ በላይ ማቅረብ የምችሉ፣
7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከጋርዱላ ዞን ገቢዎች ዩኒት ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል መግባት አለባቸዉ።
8. ተጫራቾች የገቡትን ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማዘጋጀት በሁለት የተለያዩ ፖስታ በማሸግ ኦርጅናሉ ላይ ኦርጅናል ኮፒው ላይ ኮፒ ብሎ በመፃፍ ፊርማና ማህተም በማሳረፍ በዚህ ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በ16 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ውስጥ እስከ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው 16ኛው ቀን መደበኛ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይገባል።
9. ጨረታው በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ክፍል ከረፋዱ 4፡30 ላይ ይከፈታል።
10. ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸዉ በሰዓቱ ያለመገኘት የጨረታዉን አከፋፈት አያስተጓጉልም፤
11. የጨረታዎቹ አሸናፊዎች ተለይተዉ ከተገለፀላቸዉ ከ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ አሸናፊዎች የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መግባት አለባቸው። ተሸናፊዎች ደግሞ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ መዉሰድ ይችላሉ።
12. መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ 09 20 97 83 89/ 09 26 23 82 09 ደውለዉ መጠየቅ ይችላሉ
በደቡብ ኢ/ክ/መንግሥት የጋርዱላ ዞን
ፋይናንስ ፕላን ልማት መምርያ
Tender details
- Deadline: 2026-05-12
- Publishing entity: Gardula Zone Finance Office
- Bid bond: 40,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Apr 27, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.