Garage and vehicle maintenance

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ማለትም ሀርድ ቶፕ ፒካፕ ሲንግል ጋቢና D4D ሂኖ መኪና አንቡላንስ መኪኖች በጨረታ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

መለያ ቁጥር GGWW/0002/2019

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያቤቶች አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ማለትም፡- ሀርድ ቶፕ ፒካፕ ሲንግል ጋቢና D4D ሂኖ መኪና አንቡላንስ መኪኖች በጨረታ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች

1. የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ የቫትና የቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. የጋራዥ ተሽከርካሪ ጥገና የምስክር ወረቀት በኦላይን /online/ ሲስተም የተመዘገበ መሆን አለበት፡፡

3. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙትን ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መምጣት አለባቸው፡፡

4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20ኛው ተከታታይ የስራ ቀናት 8፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 100 አንድ መቶ/ ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመቅረብ የጨረታው ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ዶክመንት ሲያቀርቡ፡ ሀ/ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት እና ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒውን ኮፒ በማድረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በሰም በማሸግ ከላይ የተጠቀሱት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 20000(ሀያ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በሰም ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ ፋይናንሻል ዶከመንት በሚል በመለየት ፡ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ሀያ/ ተከታታይ የስራ ቀናት ከገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. የጨረታው ማስከበሪያ ሲፒኦ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም መሰራት አለበት፡፡

7. የጨረታው ሰነድ 20ኛው ተከታታይ የስራ ቀናት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ ከቀኑ 8፡30 ደግሞ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

8. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡-

1. በግዢ ኤጀንሲ በዘርፉ ማስጠንቀቂያ የተሰጠባቸው ድርጅቶችም መወዳደር አይችሉም

2. ተጫራቾች የጥገና የጥራት ችግር ያለባቸው መሆናቸው በቴክኒክ ጥራት ኮሚቴ ከተረጋገጠ ውል የምናቋርጥ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

3. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0113 360 162 / 0113 360 146

የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-31
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20ኛው ተከታታይ የስራ ቀናት 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-31 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20ኛው ተከታታይ የስራ ቀናት 8፡30 ሰዓት
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: Gurage Zone Gedebano Gutazer Welene Woreda FEDB
  • Bid bond: 20,000.00 ብር
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 08, 2026)
  • Posted at: 2026-08-08T07:50:30.000Z
← Back to all tenders