Garage and vehicle maintenance

በቡኖ በደሌ ዞን ጮራ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በ2019 የበጀት አመት በጮራ ወረዳ ውስጥ ለሚገኙ መ/ቤቶች የተለያዩ የመኪና አካላትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር WM/A/C 06/2018

በቡኖ በደሌ ዞን ጮራ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በ2019 የበጀት አመት በጮራ ወረዳ ውስጥ ለሚገኙ መ/ቤቶች የተለያዩ የመኪና አካላትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. ከሚሰሩት (የሚጠገኑት) ተሽከርካሪዎች ጋር ተዛማጅነት ያለው ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው፡፡
  2. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  3.  በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
  4. ከሚያቀርቡበት ጠቅላላ ዋጋ 5% /አምስት ፐርሰንት/ በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ /CPO/ ማቅረብ የሚችል፡፡
  5.  አሸናፊ ተጫራቾች ለመልካም ስራ አፈጻጸም የጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር ፐርሰንት) ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  6. ጨረታው በአየር ላይ የሚውለው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ15 የሥራ ቀናት ሲሆን በቀን 1/12/2018 ዓ.ም በ4:00 ሰዓት ላይ አስገብተው በ22/12/2018 ዓ.ም 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጮራ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ይከፈታል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 1079 (አንድ ሺህ ሰባ ዘጠኝ ብር) በቴሌ ብር አካውንት በመክፈል ከጮራ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ገቢ ያረጉበትን ደረሰኝ በመውሰድ ከጮራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 /አምስት/ መግዛት ይቻላል፡፡
  8.  ከጠቅላላ ስራ(ጥገና) ዋጋ 3 ፐርሰንት ለመቁረጥ ፍቃደኛ የሆነ፡፡
  9. ለአሸናፊው ድርጅት ተሽከርካሪዎችን በድርጅቱ አድራሻ እናቀርባለን፡፡
  10.  አሸናፊው ድርጅት የሚጠግናቸውን ተሽከርካሪዎችን ኦሪጂናል ዕቃዎችን የመለወጥ ግዴታ አለበት፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ ዋጋ በትክክል በመሙላት በሁለት በተለያዩ ፖስታዎች ኦሪጂናል እና ኮፒውን በማሸግ ማቅረብ አለበት፡፡
  12. የታደሰ የንግድ ፍቃድ ኦሪጂናል እና ኮፒ፣ የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ ኦሪጂናል ኮፒ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ መሆኑን ማስረጃ ኦሪጂናል እና ኮፒ፣ የቲን ተመዝጋቢነት ማስረጃ ኦርጂናል እና ኮፒ እና ሌሎችንም የተለያዩ ደጋፊ ማስረጃዎችን ኦሪጂናል እና ኮፒውን በሁለት የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ ማቅረብ አለበት፡፡
  13. ሲፒኦ /CPO/ ለብቻው በታሸገ አንድ ፖስታ መቅረብ አለበት፡፡
  14. ማንኛውም ውድድር የሚከናወነው በነጠላ ዋጋ ይሆናል፡፡
  15. ተሽከርካሪዎችን ለማስገባት የቦታ ርቀት ወሳኝ ስለሆነ ተወዳዳሪዎች ከወረዳችን ከተማ ቢያንስ ከ200 ኪሎ ሜትር በላይ መራቅ የለባቸውም፡፡
  16.  ዋስትና መስጠት የሚችል መሆን አለበት፡፡
  17. ተጫራቾች አንዱ በሌላው ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ መሆኑን እንገልፃለን፡
  18. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብት አለው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- ጮራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

የስልክ ቁጥር 04 73 37 06 11/ 047 337 00 45 / 09 10 04 99 72

በቡኖ በደሌ ዞን ጮራ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-28
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአየር ላይ የሚውለው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ15 የሥራ ቀናት ሲሆን በቀን 1/12/2018 ዓ.ም በ4:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-28 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በአየር ላይ የሚውለው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ15 የሥራ ቀናት ሲሆን በቀን 1/12/2018 ዓ.ም በ4:00 ሰዓት ላይ አስገብተው በ22/12/2018 ዓ.ም 4:30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Buno Bedele Chora Woreda FEDB
  • Bid bond: 5%
  • Bid document price: 1079.00 (አንድ ሺህ ሰባ ዘጠኝ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 07, 2026)
  • Posted at: 2026-08-07T07:05:52.000Z
← Back to all tenders