በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየካ ክፍለ ከተማ የየካ መሳለሚያ ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት ዓመት አላቂ እና ቋሚ የህክምና እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደተሞከረዉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየካ ክፍለ ከተማ የየካ መሳለሚያ ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት ዓመት የ2ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ በድጋሚ የወጣ፡፡

1.6214 አላቂ እና ቋሚ የህክምና እቃዎችን ሎት አንድ CPO 10000 (አስር ሺህ ብር ) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ግለሰቦች እና ድርጅቶች በጨረታዉ እንዲሳተፉ ይጋብዛል

1. ከላይ በተራ ቁጥር 1 በሎት 1 የተከፈሉትን ዕቃዎች አግባብነት ያለው ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣የንግድ የምስክር ወረቀት፣የዘመኑን ግብር የከፈሉና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚችሉ በዕቃ አቅራቢዎች የተመዘገቡ እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡

2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የካ መሳለሚያ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 በመምጣት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ በተ.ቁጥር 1 የተጠቀሰውን ሎት በመ/ቤቱ ስም የተሰራ በ(CPO) ወይም በደብዳቤ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

4. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

5. ተጫራቾች ለየአንዳንዱ ዕቃ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ፋይናሻል ኦርጂናል እና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በየሎቱ በማሸግ ሙሉ አድራሻውን በመግለጽ የካ መሳለሚያ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡

6. የጨረታ ሰነዱ የሚዘጋው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እያሳወቅን የሚከፈትበት 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።

7. ጤና ጣቢያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. የጨረታ ሰነዱ ከመመሪያው ውጭ ሁሉም ሳይገነጠል መመለስ አለበት ሁሉንም የጨረታ ሰነድ ያልመለሰ መወዳደር አይችልም፡፡

አድራሻችን ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ አንድ ፌርማታ 200 ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ፡

ለተጨማሪ መረጃ ስ/ቁጥር 0118656665

በየካ ክፍለ ከተማ የየካ መሳለሚያ ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-08
  • Publishing entity: የየካ መሳለሚያ ጤና ጣቢያ
  • Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺ ብር)
  • Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: Apr 27, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders