የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት ሲጠቀምባቸው የነበር ቋሚ እቃዎች (ንብረቶች) በመለየት በድጋሚ መጠቀም ባለመፈለጉ ምክንያት በሁለተኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ገቢዎች ቢሮ 002/2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንብረት አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 10/2003 አንቀጽ 4 ንኡስ አንቀጽ 24 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት ሲጠቀምባቸው የነበር ቋሚ እቃዎች (ንብረቶች) በመለየት በድጋሚ መጠቀም ባለመፈለጉ ምክንያት በሁለተኛ ዙር የግልጽ ጨረታ በማውጣት ከዚህ በታች የተገለፀው የንብረት ስምና የንብረቱ ዓይነት ማለትም፦
|
ተቁ |
የንብረቱ ስም |
ብዛት |
|
1 |
ተሽከርካሪ ወንበር |
80 |
|
2 |
የእንግዳ ወንበር |
30 |
|
3 |
ፋይል ካቢኔት |
33 |
|
4 |
ሼልፍ |
4 |
|
5 |
ወርክስቴሽን (የተፈታታ) |
21 |
|
6 |
ላተራል |
7 |
|
7 |
ጠረጴዛ የተበተነ |
50 |
|
8 |
ኮፊ ቴብል |
4 |
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከላይ የተጠቀሱትን ሀብቶች ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ቢሮው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ሁሉ የጨረታ ሠነድ በመግዛት እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፦
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ቅዳሜን ጨምሮ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 11:30 የጨረታ ሰነድ በመግዛት መግዛት ይችላል።
2. ለጨረታ የቀረቡ ያገለገሉ ንብረቶች የሚገኙበት አድራሻ አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አዲስ አበባ ቁጥር 3(ሰአሊተምህረት)
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲያስገቡ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00/ ሀምሳ ሺህ ብር/ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ስም በCPO አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የነጠላ ዋጋ ቢያቀርቡም ውድድሩ የሚካሄደው በጥቅል ዋጋ ስለሆነ በዚሁ መሰረት ማስገባት አለባቸው።
5. ተጫራቾች በቅርንጫፍ ጽፈት ቤቱ በስተጀርባ ንብረቱን በአካል ተገኝተው ማየት ይችላሉ።
6. የጨረታው አሸናፊዎች ውል ከፈፀሙበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 5 ቀን ውስጥ ሙሉ ክፍያ ፈፅመው ሙሉ እቃውን ማንሳት አለባቸው።
7. ተጫራቾች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማስገባት አይችሉም።
8. ጨረታው በሚያበቃበት ከ11:30 ታሽጎ በነጋታው ተጫራቾች በተገኙበት ከጠዋቱ 4:30 የሚከፈት ስለሆነ በሰዓቱ ተገኝተው የጨረታ ሂደቱን መከታተል ይችላሉ።
9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
አድራሻ፤ - ሰነድ ለመግዛት አፍሪካ ህብረት ፊትለፊት አማጋ ህንፃ አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 የግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ውስጥ ሲሆን ንብረቶቹ የሚገኙበት ሰአሊተምህረት ወይም አዲስ አበባ ቁጥር 3 ገቢዎች ቢሮ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ
የንብረት አስተዳደር ቡድን
(ስልክ ቁጥር +251-011-557-5732)
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-05-07
- Publishing entity: Addis Ababa City Administration Revenues Bureau
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Published: Apr 27, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.