በደ/ኢ/ክ/መንግሥት የግብርና ቢሮ የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የማይሰጡ ዕቃዎችን የንብረት አስወጋጅ ኮሚቴ ከለዩት ዕቃዎች ውስጥ አንዱ የኤሌክትሪክ ኬብል ሲሆን እንዲወገድ ባቀረቡት መሠረት በግልጽ ሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ ግልጽ የሐራጅ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር 006/ 2018

በደ/ኢ/ክ/መንግሥት የግብርና ቢሮ የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የማይሰጡ ዕቃዎችን የንብረት አስወጋጅ ኮሚቴ ከለዩት ዕቃዎች ውስጥ አንዱ የኤሌክትሪክ ኬብል ሲሆን እንዲወገድ ባቀረቡት መሠረት በግልጽ ሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች/ግለሰቦች /የመንግሥት ተቋማት/

1. የዕቃው ዓይነት የኤሌክትሪክ ኬብል ነው።

2. ሽያጩ የሚከናወነው በወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲሆን ንብረትነቱ የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ነው።

3. አድራሻ፤ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በወላይታ ዞን ሶዶ ግብርና ኮሌጅ በማርካቶ ክፍለ ከተማ ፋና ቀበሌ ነው።

4. የኤሌክትሪክ ኬብል ዓይነት 3*70*35 mm2 የሆነ ብዛት በጥቅል ከ400 ሜትር በላይ ነው። ነገር ግን ተጫራች የአንድ ሜትርን ዋጋ ይጫረታል።

5. ተጫራች ዕቃውን ለማየት የሚፈልግ ከሆነ እስከ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ድረስ በመቅረብ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየትኛውም በሥራ ቀን በሥራ ሰዓት ወደ ፋይናንስ ቢሮ ቀርቦ በመጠየቅና ማየት ይችላል።

6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ15 ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው 16ኛ የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ዕቃው ባለበት ይካሄዳል። 16ኛው የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ በሚውለው የስራ ቀን ይካሄዳል።

7. ጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 30,000.00/ሰላሳ ሺህ ብር/ ማስያዝ ይጠበቅበታል። በሌላ አማራጭ የሚቀረብ ተቀባይነት የለውም።

8. አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነትን በተቋሙ ሀላፊ ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀን ውስጥ ገንዘቡን ሙሉ በሙሉ በግብርና ኮሌጅ አካውንት ገቢ ማድረግ እና ዕቃውን ማንሣት ይኖርበታል።

9. ኮሌጁ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስ.ቁጥር 046 551 3984 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል።

በደ/ኢ/ክ/መንግሥት የግብርና ቢሮ የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-12
  • Publishing entity: Wolaita Sodo Agricultural College
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Published: Apr 27, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders