በሠላም ማስከበር ማዕከል የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ት/ቤት ንብረትነታቸው የማሰልጠኛ ት/ቤቱ የሆኑ የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶች ሽያጭ ግልጽ ጨረታ የጨረታ ቁጥር CON/TRS/AN./PRO 04/2018

በሠላም ማስከበር ማዕከል የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ት/ቤት ንብረትነታቸው የማሰልጠኛ ት/ቤቱ የሆኑ የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፤

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. በጨረታው የሚወዳዳሩ ተጫራቾች የኢትዮጵያ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ይሄንኑ የሚያረጋገጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሆነ ግለሰብም ሆነ ድርጅት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  3. በአዲስ አበበና አካባቢዋ የሚገኙ ተጫራቾች በአዲስ አበባ በጃን ሜዳ በሚገኘው የሰላም ማስከበር ማዕከል ግዥ ቢሮና አንዲሁም ድሬዳዋና አካባቢው የሚገኙ ተጫራቾች በሁርሶ የሚገኘው በሰላም ማስከበር ማዕከል የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ት/ቤት ግዥ ቢሮ ቁጥር 26 በመምጣት የንብረቶችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት 200.00 (ሁለት መቶ ብር ) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 አስከ 11፡00 ሰዓት ልዩልዩ ንብረቶችን ሁርሶ በሚገኘው በሰላም ማስከበር ማዕከል የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ት/ቤት በመገኘት በአካል መመልከት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረቶች የጨረታውን መነሻ ዋጋ ተሰልቶ ማስያዝ አለባቸው። ለሎት አንድ 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) ለሎት ሁለት 32,000.00 (ሰላሳ ሁለት ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በማሰልጠኛ ት/ቤቱ ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨኰፕ በማድረግ በሰላም ማስከበር ማዕከል የኮንቲጀንት ማሰጠኛ ት/ቤት ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 8፡15 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10ኛ ቀን ማለትም ሚያዝያ 29/2018 ከቀኑ 8፡15 ታሽጎ በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሁርሶ በሚገኘው በሰላም ማስከበር ማዕከል የኮንቲጀንት ማሰጠኛ ት/ቤት ትንሿ አዳራሽ ይከፈታል። እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ፍቃድ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም።
  7. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለጸላቸው ከሰባት የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ መክፈቴ ይኖርባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ከፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
  8. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በጨረታ ሰነዱ የተገለፁትን አሟልቶ መገኘት ነው፡፡ በሰነዱ የተቀመጡትን ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።
  9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፋባቸውን ንብረቶች ሙሉ ክፍያ ከፍኰ እስከሚወስድ ድረስ ከውል አተገባበር ዋስትና የሚሆን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ (10%) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት።
  10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመከፈል ንብረቶቹን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው።
  11. ማሰልጠኛ ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 025-447-0115 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

በሰላም ማስከበር ማዕከል የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-07
  • Publishing entity: Ministry of Defense
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Apr 28, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders