የኢትዮጵያን ሸ/ኃላ/የተ/የህ/ስ/ማህበር የማህበሩን የ2015 በጀት ዓመት መነሻ በማድረግ የ2016 እና የ2017 በጀት ዓመት የኦዲት ስራን መስፈርቶች የሚያሟሉ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ዓመታዊ ሂሳብ ሪፓርቱን ኦዲት ማሰራት ይፈልጋል
Description
የኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵን ሸኃላ/የተ/የህ/ስ/ማህበር የማህበሩን የ205 በጀት ዓመት መነሻ በማድረግ የ2016 እና የ2017 በጀት ዓመት የኦዲት ስራን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ዓመታዊ ሂሳብ ሪፓርቱን ኦዲት ማሰራት ይፈልጋል።
ተጫራቾቹ፡-
1. የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ወይም እሱ ከሚወክለው አካል ሂሳብ ለመመርመር የሚያስችለውን የሙያ ፊቃድ ያገኘ እና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መቅረብ የሚችል/የምትል።
2. ተጫራቾቹ በአገሪቱ ህግ መሰረት የኦዲት ስራ ለመስራት የሚያስችል በዘርፉ የታደሰ የሙያ ፈቃድ፤ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሠርትፍኬት፣ እንዲሁም ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን የመንግስት ግብር ስለመክፈሉ መረጃ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
3. የኦዲት ስራ ለመስራት የሚያስችልና ከተገቢው ባላስልጣን ያገኘውን የሙያ ፈቃድ እና የሙያ ብቃት ማረጋጋጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፤
4. የህብረት ስራ ማህበራት ሂሳብ ምርመራ በተመለከተ ከፌዴራል ህብረት ስራ ኤጄንሲ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኤጄንሲ ወይም ከሌሎች ህጋዊ አካላት ስልጠና የወሰደና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ቢሆን ይመረጣል፤
5. በመሰል ማህበራት ውስጥ የኦዲት ስራ ስለመስራቱ የልምድ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ፤
6. ተጫራች ቀጥሮ የሚያሰራቸውን ባለሙያዎች ሂሳቡን ለመመርመር የሚያስችላቸውን ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
7..ተጫራቾች የመልካም ስራ አፈፃፀም መረጃዎቻቻውን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤
8. ማህበሩ ኦዲት ስራ ያቀረበው ሰነድ ብዛት 22 ፎልደር ወጪና 25 ፎልደር ገቢ በድምሩ 47/ አርባ ሰባት/ ።
9.ተጫራቾች ስራውን የሚያጠናቅቁበትን ቀን በግልፅ መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
10. ተጫራች ኦዲት ስራውን የሚሰራበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ስርዝ ድልዝ ሳይደረግ ግል በሆነ መልኩ በታሸገ ኢንቨሎፕ ለዚሁ ስራ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂ ከወጣበት በ10 የስራ ቀናቶች ውስጥ ቅዳሜ እስከ ቀኑ 6፡30 ድረስ መጠቀም ይችላሉ።
11. ጨረታው በ10ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 4፡15 ላይ ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የኢትዮጵን ሸ ኃላ/የተ/የህ/ስ/ማህበር ግዢ ክፍል ይከፈታል። 10ኛው ቀን በዓል ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ቀን ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ላይገኝ ቢቀር ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉለውም።
12. ተጫራቾቹ የተጫረቱበትን የጨረታ ውል ማስከበሪያ ዋጋ 10% የኢትዮጵን ሸ/ኃላ/የተ/የህ/ስ/ማህበር ስም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ ሲፒኦ ወይንም ቢዲ ቦንድ ማሰራት ወይንም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000280343548 ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
13. በጨረታ አፈፃፀሙ ቅር የተሰኘ አካል በቅሬታው መሰረት የሆነውን የመጨረሻ ውሳኔ ካወቀበት ወይም ማወቅ ከነበረበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ውስጥ በፁሁፍ ለተቋሙ ማናጀር ማቅረብ ይጠበቅበታል። ሆኖም ከተጠቀሰው ቀን በኃላ፤ የሚቀርበው አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ።
14. ተጫራቾቹ በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማስገባት ከጨረታ ውድድሩ ያሰርዛል።
15. አሸናፊው ድርጅት የኢትዮጵን ሸ ኃላ/የተ/የህ/ስ/ማህበር ጋር ውል በመግባት መስራት ይጠበቅበታል።
16 ከላይ ከተዘረዘሩት መስፈርቶችን አሟልቶ በዋጋ እኩል ያመጣ ተወዳዳሪ ለማህበሩ አባል ከሆነ በቅድሚያ ይሰጣል። የማህበሩ አባል ካልሆኑ በዕጣ ይለያል።
17. የሸማች ህ/ስ/ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ከ49 ማዞሪያ ወደ አራብሳ በሚወስደው አስፓልት ሎሚ ከለር 40/60 ኮንደሚኒየም መጨረሻ በግምት 200 ሜትር ተጉዘው ኢትዮጵያን አየር መንገድ ሰራተኞች የጋራ መኖሪያ ቤቶች ቅጥር ግቢ ውስጥ ያገኙታል።
ለበለጠ መረጃ፤ በስልክ ቁጥር፡- 09-11-29-17-17/ 09-30-33-33-98 /09-12-97-51 94 ወይም 09-07-50-9707ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የኢትዮጵን ሸ/ኃላ/የተ/የህ/ስ/ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-05-08
- Publishing entity: የኢትዮጵያን ሸ/ኃላ/የተ/የህ/ስ/ማህበር
- Bid bond: 10%
- Published: Apr 28, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.