የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የጤና መድህን ድርጅት፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት፣ የእንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን፣ የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ጽ/ቤት፣ የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ፣ አክሱም ዩኒቨርሲቲ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሆኑ የኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻዎች ባሉበት ቦታና

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር PPN/NVP-10FBI/09/08/2018

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የጤና መድህን ድርጅት፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት፣ የእንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን፣ የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ጽ/ቤት፣ የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ፣ አክሱም ዩኒቨርሲቲ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሆኑ የኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻዎች ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላል።

1. በጨረታው ላይ የሚወዳደር ተጫራች በኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻ አወጋገድ ከፌዴራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በዘርፉ ፈቃድ የተሰጠው ሲሆን የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ሲመጣ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ፈቃድ እና መታወቂያ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።

2. ተጫራቾች 6 ኪሎ በሚገኘው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ግዥና ፋይናንስ ስራ አስፈፃሚ 01.0 ቢሮ በመምጣት የንብረቶች ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመንግሥት ግዥ አገልግሎት የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000003785018 ላይ በቴሌ ብር እና ሲቢኢ ብርን በመጠቀም የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹን ከላይ በተጠቀሱት መ/ቤቶች በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረቶች ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው። የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል።

5. የጨረታው የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋ፣ የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይሆናል። ይሁንና የንብረቶቹን የመነሻ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) ነገር ግን ብር 100,000/አንድ መቶ ሺ ብር ያልበለጠ ያላስያዘ እንዲሁም በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።

6. የጨረታ ማስገቢያ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ነገር ግን የመከፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ላይ ካልሆነ (ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ) ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ላይ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስቀረውም።

7. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 (ሰባት) የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መከፈል ይኖርባቸዋል። ይሁንና ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።

8. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ንብረቶች ሙሉ ክፍያ ከፍለው እስከሚወስዱ ድረስ ለውል አተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው።

9. አገልግሎቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል።

10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በ10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው።

11. አሸናፊው በዚህ ጨረታ ላይ ያልተጠቀሱ መ/ቤቶችንና የኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻዎችን ጭምር በውል በማካተት እስከ አንድ ዓመት ድረስ በዚህ ጨረታ ባሸነፈበት ዋጋ እንዲያነሳ ይደረጋል፡፡ ሆኖም አዋጪ ካልሆነ አገልግሎቱ ማራዘሙን ሊያስቀረው ይችላል።

12. አገልግሎቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- የኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት 6 ኪሎ የካቲት 12 ሰማዕታት ሐውልት አደባባይ ፊት ለፊት

ለበለጠ መረጃ፡- የተቋማችንን ድህረ-ገጽ www.pps.gov.et ይጎብኙ

የፌዴራል መንግስት ግዥ አገልግሎት

አዲስ አበባ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-18
  • Publishing entity: ፌዴራል መንግስት ግዥ አገልግሎት
  • Bid bond: 2% ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Apr 28, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders