Garage and vehicle maintenance
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የመኪና እና ማሽነሪዎች GSE/GTV/ ሞተር እና የተለያዩ የሜካኒካል ክፍሎች የጥገና እና የማሻሻያ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በረጅም ዓመት ኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር:
SSNT-T612
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የመኪና እና ማሽነሪዎች GSE/GTV/ ሞተር እና የተለያዩ የሜካኒካል ክፍሎች የጥገና እና የማሻሻያ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በረጅም ዓመት ኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ፍቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 03 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የጨረታ ቁጥሩን፣ የድርጅታቸውን ስምና ስልክ ቁጥር ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን በነጻ በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) “በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ” ስም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል ግንቦት 03 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ9፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ፡-
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
ስልክ ቁጥር፡ +251-115-17-89-18
ኢ-ሜይል: [email protected]
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
Tender details
- Deadline: 2026-05-11
- Publishing entity: Ethiopian Airlines Group (ETG)
- Bid bond: 15,000.00 ብር
- Published: Apr 28, 2026