የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ሕግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ሕግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በ28/08/2018 እና 01/09/2018 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣሎት የምትፈልጉት የእቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እንዲመጣሎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
የጨረታ መስፈርቶች:-
1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክሰ ምዝገባ ሰርተፍኬት የዘመኑን ግብር የከፈለ ሰለመሆኑ ክሊራንስ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክሰ እንቅስቃሴያቸውን ለታከሰ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል።
2. ተጫረ ቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስክ ቀን በ28/08/2018 እና 01/09/2018 ዓ/ም እስከ ጠዋቱ 3፡45 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ።
3. ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (cpo) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሰም ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
4. ተጫራቾች በሚከተሉት የጨረታ ቀናት (እስኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ፡፡
|
ተቁ |
የጨረታ ቦታ |
የጨረታው ዓይነት |
ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች |
የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1. |
ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት |
ግልጽ ጨረታ እና በሐራጅ |
ጫማዎች አልባሳት፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የሞባይል ቀፎና አሰሰሪ ኤሌክትሮኒክስ፣ ምግብ ነክ፣ የስፖርት እቃዎች፣ የእጅ ሰዓት ኮስሞቲክስ ፌሮ ብረት ቆርቆሮ፣ጥቅል ብረት መነፅር፣ ጌጣ ጌጦች ጠፍጣፋ ብረት ላሜራ የወዳደቁ ብረቶችና ፕላስቲኮች እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች |
ለግልጽና ለሐራጅ ጨረታ በ28/08/2018 እና 01/09/2018 ዓ/ም እስከ ጠዋቱ 3:45 |
ለግልጽ ጨረታ በ28/08/2018 እና 01/09/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4:00 ሲሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ ጊዜ በ28/08/2018 እና 1/09/2018 ዓ/ም 5፡00 ሰዓት ይሆናል። |
5. የጨረታ መክፈቻ ቦታ፡- በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
6. በጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋሰትና ያስያዙት (c.p.o) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
7. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸዉ በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ዉሰጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖርበታል።
8. ከላይ በተ ቁ7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሸኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
9. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በጉምሩክ ኮሚሽን የአዋሽ ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-09
- Publishing entity: Ethiopian Revenue & Customs Authority Awash Branch
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: Apr 29, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.