በከልቻ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ያገለገሉ ኤሮ ትራከር ተሳቢ ተሽካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

በከልቻ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር በድጋሜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 3/2026

በከልቻ  ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ያገለገሉ ኤሮ ትራከር ተሳቢ ተሽካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም

ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እኤአ ዘወትር በሥራ ሰዓት: ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡15 ከሰዓት በኋላ 7፡30 አስከ 11፡15 ሰዓት ድረስ እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ብቻ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል አዳማ ሶደሬ መንገድ ከሚገኘው ዋና መ/ቤታችን ፋይናንስ መምሪያ ካሸር ቢሮ ወይም አዲስ አበባ ካዲስኮ ህንፃ ፊት ለፊት በሚገኘው ከማስተባበሪያ ጽ/ቤታችን መውሰድ ይችላሉ።

2 ማንኛውም ተጫራች ለሚመረተው ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ በገዛው የጨረታ ሰነድ ላይ በተቀመጠው የጨረታ መነሻ ዋጋ መሰረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን 20% በባንክ በተመሰከረለት CPO በጨረታው መክፈቻ ሰአት ጨረታው ከመጀመሩ በፊት ማስያዝ የሚኖርበት ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያውም ለተሽናፊ ተጫራቾች ወዲያውኑ የሚመለስ ሲሆን፤ የአሸናፊው ተጫራች ሙሉ ክፍያውን ሲከፍል የሚመለስ ይሆናል።

3 ጨረታውም አርብ እ.ኤ.አ 24/04/2026 ወይም ከሚያዝያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. ከሰአት በኋላ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዳማ በሚገኘው የአ/ማህበሩ ዋና መ/ቤት ቅጥር ግቢ በሰራተኞች ክበብ አዳራሽ ውስጥ በግልጽ ተከፍቶ ለሽያጭ የቀረቡ ተሳቢ ተሽከርካሪዎች ተሸጠው እስኪጠናቀቁ ድረስ በየሳምንቱ አርብ አርብ ቀን ከሰአት በኋላ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ጨረታው ይቀጥላል።

4. በጨረታው ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10 ቀናት ውስጥ ለአ/ማህበሩ ገቢ ማድረግ ያለበት ሲሆን ይህንን ያላደረገ ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለአ/ማህበሩ ገቢ ሆኖ ተሽከርካሪው በድጋሜ ለጨረታ የሚቀርብ ይሆናል።

5. በጨረታው ያሸነፈ ተጫራች ያሸነፈበትን ተሽከርካሪ ሙሉ ክፍያ ከፈጸመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተሽከርካሪውን የማንሳት ግዴታ ያለበት ሲሆን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ተሽከርካሪውን ለማንሳት ያልቻለ የጨረታ አሸናፊ የተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ተሽከርካሪውን ለማንሳት ያልቻለ የጨረታ አሸናፊ የተሰጠው የጊዜ ገደብ ከተጠናቀቀበት ጊዜ ጀምሮ ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ በቀን ብር 300.00 / ሦስት መቶ ብር የማቆያ ኪራይ ክፍያ የመክፈል ግዴታ አለበት።

6. ተሽከርካሪዎቹ የሚፈለግባቸው ማንኛውም ቀረጥና ውዝፍ እዳ ቢኖር በአ/ማህበሩ ይሸፈናል። ነገር ግን የስም ማዛወሪያን እና የቦሎ ክፍያ በገዢው በኩል ይከፈላል።

7. ተጨማሪ ዝርዝር የሽያጭ ሁኔታና የጨረታ መመሪያ በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ላይ በግልጽ ይቀመጣል።

8. ኤ ማኀበሩ የተሻለ አማራጮችን ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ:- በስልክ ቁጥር 0221-11 17 91 ናዝሬት 0913 09 10 03 ወይም 0114-43 13 48 ይደውሉ።

በከልቻ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-05-07
  • Publishing entity: BeKelcha Transport Association
  • Bid bond: 20%
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published: Apr 29, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders