የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ለማሽነሪዎች እና ከባድ መኪና የሚውል መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ መስፈርቱን ከሚያሟሉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ለሁለተኛ ዙር የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር፡-ሲ/መ/ባ/001/2018
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ መንገድ ለሚያሰራቸው ማሽነሪዎች እና ከባድ መኪና የሚውል መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ መስፈርቱን ከሚያሟሉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ሎት |
የግዥ ዓይነት |
|
1 |
የማሽነሪ መለዋወጫ ግዥ |
|
2 |
የከባድ መኪና መለዋወጫ ግዥ |
በዚሁ መሠረት፡-
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎትጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ወይም የአገልግሎት የሥራ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸውን የሚያሳይ ሰርተፍኬት፤ የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈጸም ቃል መግቢያ ደብደቤ በማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10(አስር) ተከታታይ ቀናት ከባለሥልጣኑ መቤት ግዥ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
- አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን እስከ ከ11ኛ ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ይሆናል ጨረታው በዚያ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
- ተጫራቾች የጠቅላላ ዋጋ 0.5% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ከተረጋገጠ ቼክ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዶች ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታችውን ማቅረብ አለባቸው።ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመርያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማሰከበርያ Bid Security ፋይናሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንድሁም ቴክንካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒ ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ተካተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሮክቶሬት ከፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሠነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት። ከላይ የተጠቀሰው ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የእረፍት ወይም የህዝብ በዓል ቀን ሆኖ ከዋለ በቀጣይ በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
- በጨረታ ሰነድ ላይ የተጠቀሱትን የጨረታ መመሪያ እና ህጎች አለማክበር በመጫረቻ ሰነዶቻቸው በሁሉም ገጽ ላይ ማህተምና ፊርማ ያለማድረግ እና ያልተፈረመበት ሰረዝ ድልዝ ያለበት የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ በባለስልጣኑ መ/ቤት አደራሽ ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡-ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፈል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡- 046 212 8446
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን
Tender details
- Deadline: 2026-05-11
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን እስከ ከ11ኛ ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-11 14:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን እስከ ከ11ኛ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Sidama Roads Authority
- Bid bond: 0.5%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Apr 30, 2026
- Posted at: 2026-04-30T07:47:11.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.