የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ንብረትነታቸው የቅ/ጽ/ቤቱ የሆኑ የተለያዩ የፈርኒቸር እቃዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ያገለገሉ የተለያዩ ፈርኒቸሮች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ECCJBO/01/2018

በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ንብረትነታቸው የቅ/ጽ/ቤቱ የሆኑ የተለያዩ የፈርኒቸር እቃዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት ቀርበው በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፣

2. የንብረቶችን ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በመምጣት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣

3. ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 5፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ የጨረታ ሰነድ ገዝተው እቃዎችን በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ተገኝተው መመልከት ይችላሉ፣

4. ተጫራቾች በሚገዙት ዕቃዎች የጨረታ የመሸጫ መነሻ ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በሚዘጋበት ቀን እስከ 4፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል፣

5. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ጠቅላላ ዋጋ እና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን መስፈርቶች አሟልቶ መገኘት ነው፣

6. የጨረታው የመሸጫ የመነሻ ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ (10%) ያልያስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች መስፈርቶችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፣

7. የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ወይም ሲ.ፒ.ኦ. ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ የተዘጋጀ መሆን ይኖርበታል፣

8. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚዘጋና የሚከፈት ሲሆን፤ ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፣

9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ውል መፈረም እና ያሸነፉበትን ዋጋ ሙሉ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ተወርሶ ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል።

10. ቅ/ጽ/ቤቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በሥሙ ወይም በሕጋዊ ተወካዩ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል።

11. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በከፈሉ በ10 ቀናት ውስጥ ንብረቶቹን የማንሳት ግዴታ ያለባቸው ሲሆን፣ ይህ መሆን ካልቻለ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ተወርሶ ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል፣ ዕቃውም በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል፣

12. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 09 15 74 87 90 ወይም 09 13 22 04 73 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣

13. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን መቀበል ወይም አለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

አድራሻችን፡- ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 05

ተጨማሪ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 09 15 74 87 90 ወይም 09 13 22 04 73

በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-14
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: Apr 30, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders