አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ የሰራተኞች የደንብ ልብስ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ

ቁጥር AMFI 11/2018

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ የሰራተኞች የደንብ ልብስ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ፡

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ ሆነው የዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን የተሠጠ የምስክር ወረቀት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ በተከፈለበት በአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ኢማ ደረሠኝ ወይም የባንክ ዋስትና እንደምርጫቸው በአንዱ ከዋናው የዋጋ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አሥር) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 (አሥራ አንድ ሰዓት) ድረስ የማይመለስ 400.00 (አራት መቶ ብር) ለአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ በአሐዱ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 0003230410101 ገቢ በማድረግ ገቢ የተደረገበትን ደረሰኝ አቅርበው ከአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ወሰን ቅርንጫፍ መውሰድ ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን የያዙ ሰነዶች የዋጋ ሰነድ ዋና እና ቅጅ ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 11ኛው ቀን ሲሆን ከጠዋቱ 4፡00 (አራት ሰዓት) ድረስ ብቻ ከአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ኣ.ማ ወሰን ቅርንጫፍ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 (አራት ሰዓት) ታሽጎ በዚያው እለት ከጠዋቱ 4፡30 (አራት ሰዓት ተኩል) ላይ በግልጽ ተከፍቶ የእቃው ዋጋ ተጫራቾችና ታዛቢዎች ባሉበት ይነበባል። የመክፈቻ ቀኑ በሳምንቱ የዕረፍት ቀናት ወይም ብሔራዊ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል። /ትክክለኛው የመክፈቻ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፅ ይሆናል።

6. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፉባቸውን የደንብ ልብስ በጨረታ ሰነዱ በተቀመጠው አግባብ በራሳቸው ሙሉ ወጪ አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ዋና መ/ቤት(ደብረ ብርሃን አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ሕንጻ) ድረስ አምጥተው ገቢ ማድረግ አለባቸው።

7. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።

8. የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ለተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በጽሁፍ በተቋሙ የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳና በደብዳቤ እንገልፃለን

9. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 637 66 68/011 637 64 57 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም


Tender details

  • Deadline: 2026-05-12
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 (አራት ሰዓት)
  • Bid opening: 2026-05-12 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 (አራት ሰዓት)
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ/ማ
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 400.00 /አራት መቶ ብር/
  • Published: May 02, 2026
  • Posted at: 2026-05-02T07:26:52.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders