ተስፋዬ ሰለሞን ዘውዴ ለቢራ ግብአት የሚሆን ገብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ተስፋዬ ሰለሞን ዘውዴ ለቢራ ግብአት የሚሆን ገብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ በመከተልና ከዚህ ጋር ተያይዞ በቀረበው መስፈርት መሰረት ተጫራቾች ይህንን ጨረታ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።
የጨረታ መመሪያ
1. ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN እና የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ተመዝጋቢ የሆኑና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ
3. ተጫራቾች በሙያው አምስት አመት እና ከዚያ በላይ ልምድ ያለውና ለትላልቅ ድርጅቶች ያቀረበና የሙያ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
4. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ቦሌ ብራስ አብኮ ህንጻ 2ተኛ ፎቅ መግዛት ይቻላል።
5. ተጫራቾች በቀረበው የእቃ ዝርዝርን መሰረት በማድረግ የሚወዳደሩበትን ነጠላ ዋጋ (unit price) በግልፅ በሚነበብ አሃዝ በማስቀመጥ በመሙላት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት 05 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ6ተኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8፡30 ሰዓት ይከፈታል። ነገር ግን የመክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም የህዝብ በዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
6. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሰውን ያህል የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ትዕዛዝ(CPO) ወይንም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በታሸገ ፖስታ አድርገው በማዘጋጀት ማቅረብ አለባቸው።
7. ተጫራቾች ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በመሙላት ቴክኒካል ፕሮፖዛል ኦርጅናል ቴክኒካል ፕሮፖዛል ኮፒ ፋናይሻል ኦርጅናል፤ፋይናሻል ኮፒ በማለት ለይተው በተለያየ ፖስታ በማድረግ፤ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም በማሳረፍ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. የጨረታ አሸናፊ ውጤት እደተገለፀ ከ7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት ተከታታይ 05 (አምስት) ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል ይፈጽማል።
9. ድርጅቱ ይህንን ጨረታ ለአሸናፊ በሚሰጥበት ጊዜ የመግዣ የነጠላ ዋጋ ሣይቀይር ብዛት በ 20% የመጨመር የመቀነስ መብት አለው።
10. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251978918915 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ተስፋዬ ሰለሞን ዘውዴ
Tender details
- Deadline: 2026-05-07
- Publishing entity: ተስፋዬ ሰለሞን ዘውዴ
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published: May 02, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.