ብራና ማተሚያ ድርጅት የተለያዩ አይነት የሠራተኞች ሙሉ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰፋት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 005/2018

ብራና ማተሚያ ድርጅት የተለያዩ አይነት የሠራተኞች ሙሉ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰፋት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የሀገር ውስጥ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

1ኛ. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ።

2ኛ. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።

3ኛ. የግብር ከፋይነት መለያ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

4ኛ. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

5ኛ. ግብር የመከፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ ክሊራንስ/ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

6ኛ. በመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በአቅራቢነት ለመመዝገባቸው ማስረጃ ያላቸው።

7ኛ. ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር አምስት መቶ (500.00) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ወሎ ሰፈር በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 26 በአካል በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

8ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 2% በሲ.ፒ.ኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

9ኛ. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማስረከቢያ ጊዜውን መጥቀስ አለባቸው።

10ኛ. ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፏቸውን ዕቃዎች ድርጅቱ መጋዘን ድረስ ማድረስ አለባቸው።

11ኛ. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 11ኛው የሥራ ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት (ከሰዓት) ድረስ በሰም በታሸገ ፖስታ ለጨረታ ማስገቢያ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች በተገኙበት ወይም ባይገኙም ጨረታው በወጣ በ11ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ በ8፡00 (ከሰዓት) ታሽጎ በ8፡30 (ከሰዓት) በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።

12ኛ. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ከወሎ ሰፈር ወደ ጎተራ በሚወስደው መንገድ 700 ሜትር ላይ በስተግራ በኩል

ስልክ ቁጥር፡- 011 442 6480

ብራና ማተሚያ ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-13
  • Publishing entity: Branna Printing Enterprise
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: May 01, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders